La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




1 ነገሥት 2:28 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በአንድ በኩል የአዶንያስ ደጋፊ፥ በሌላ በኩል ደግሞ የአቤሴሎም ተቃዋሚ የሆነው ኢዮአብ የተፈጸመውን ነገር ሁሉ ሰማ፤ ስለዚህም ሸሽቶ ወደ ጌታ ድንኳን ሄደ፤ በዚያም የመሠዊያውን ቀንዶች ይዞ ተማጠነ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከአቤሴሎም ጋራ ሳይሆን ከአዶንያስ ጋራ አሢሮ የነበረው ኢዮአብም ይህን በሰማ ጊዜ፣ ወደ እግዚአብሔር ድንኳን ሸሽቶ የመሠዊያውን ቀንድ ያዘ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በአንድ በኩል የአዶንያስ ደጋፊ፥ በሌላ በኩል ደግሞ የአቤሴሎም ተቃዋሚ የሆነው ኢዮአብ ይህን የተፈጸመውን ነገር ሁሉ ሰማ፤ ስለዚህም ሸሽቶ ወደ ተቀደሰው ድንኳን ሄደ፤ በዚያም የመሠዊያውን ቀንዶች ይዞ ተማጠነ፤

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ለሶ​ር​ህያ ልጅ ለኢ​ዮ​አ​ብም ወሬ ደረ​ሰ​ለት፤ ኢዮ​አብ ከአ​ዶ​ን​ያስ ጋር ተባ​ብሮ ተከ​ተ​ለው እንጂ ከሰ​ሎ​ሞን ጋር አል​ተ​ባ​በ​ረም፤ አል​ተ​ከ​ተ​ለ​ው​ምም ነበ​ርና። ኢዮ​አ​ብም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ድን​ኳን ሸሽቶ የመ​ሠ​ዊ​ያ​ውን ቀንድ ያዘ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ለኢዮአብም ወሬ ደረሰለት፤ ኢዮአብም አቤሴሎምን አልተከተለም ነበር ነገር ግን አዶንያስን ተከትሎ ነበር። ኢዮአብም ወደ እግዚአብሔር ድንኳን ሸሽቶ የመሠዊያውን ቀንድ ያዘ።

Ver Capítulo



1 ነገሥት 2:28
8 Referencias Cruzadas  

አቤሴሎምም በኢዮአብ ምትክ አማሳይን በሠራዊቱ ላይ ሾመ፤ አማሳይ የእስማኤላዊው የዮቴር ልጅ ነበረ፤ ዮቴርም የኢዮአብን እናት፥ የጽሩያን እኅት፥ የናዖስን ልጅ አቢግያንሰ አግብቶ ነበር።


ሠራዊቱን ሲሦውን በኢዮአብ፥ ሲሦውን በኢዮአብ ወንድም በጽሩያ ልጅ በአቢሳይ፥ ሲሦውን ደግሞ በጌታዊው በኢታይ አዛዥነት ሥር ላካቸው። ንጉሡም ለሠራዊቱ፥ “እኔ ራሴም አብሬአችሁ እወጣለሁ” አላቸው።


አዶንያስም ሰሎሞንን ፈራ፥ ተነሥቶም ሄደ፥ የመሠዊያውንም ቀንድ ያዘ።


ስለዚህ ከጽሩያ ልጅ ከኢዮአብና ከካህኑ ከአብያታር ጋር አሴረ፤ እነርሱም አዶንያስን ደገፉት።


ሰው ግን ቢደፍር፥ ባልጀራውንም በተንኮል ቢገድለው፥ እንዲገደል ከመሠዊያዬ አውጥተህ ውሰደው።


በአራቱም ማዕዘን ቀንዶችን አድርግለት፥ ቀንዶቹም ከእርሱ ጋር ወጥ ሆነው የተሠሩ ይሁኑ፤ በነሐስም ለብጠው።


በቀልና ብድራት መመለስ የእኔ ነው፤ እግራቸው የሚሰናከልበት ጊዜው፥ የመጥፊያቸው ቀን ቀርቧልና፥ የሚመጣባቸው ፍርድ ይፈጥናል።