በገለዓድ የምትገኘው የቱቢ ተወላጅ የሆነውና ኤልያስ ተብሎ የሚጠራው ነቢይ፤ ንጉሥ አክዓብን “በእኔ ቃል ካልሆነ በቀር በሚቀጥሉት ዓመቶች በምድር ላይ ጠል ወይም ዝናብ እንደማይኖር እኔ በማገለግለው በእስራኤል አምላክ፥ በሕያው ጌታ ስም እነግርሃለሁ” አለው።
1 ነገሥት 18:41 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚህ በኋላ ኤልያስ ንጉሥ አክዓብን “እንግዲህ ሄደህ እህልና ውሃ ቅመስ፤ እኔ አሁን የከባድ ዝናም ነጐድጓድ ድምፅ መቃረቡን እየሰማሁ ነው” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኤልያስም አክዓብን፣ “የከባድ ዝናብ ድምፅ ይሰማልና ሂድና ብላ፤ ጠጣም” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ ኤልያስ ንጉሥ አክዓብን “እንግዲህ ሄደህ እህልና ውሃ ቅመስ፤ እኔ አሁን የከባድ ዝናም ነጐድጓድ ድምፅ መቃረቡን እየሰማሁ ነው” አለው፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኤልያስም አክዓብን፥ “የዝናቡ ውሽንፍር እጅግ ነውና ተነሥተህ ውጣ፤ ብላም፤ ጠጣም” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኤልያስም አክዓብን “የዝናቡ ውሽንፍር እጅግ ነውና ተነሥተህ ውጣ፤ ብላም፤ ጠጣም፤” አለው። |
በገለዓድ የምትገኘው የቱቢ ተወላጅ የሆነውና ኤልያስ ተብሎ የሚጠራው ነቢይ፤ ንጉሥ አክዓብን “በእኔ ቃል ካልሆነ በቀር በሚቀጥሉት ዓመቶች በምድር ላይ ጠል ወይም ዝናብ እንደማይኖር እኔ በማገለግለው በእስራኤል አምላክ፥ በሕያው ጌታ ስም እነግርሃለሁ” አለው።
ከብዙ ጊዜ በኋላ በሦስተኛው ዓመት ጌታ ኤልያስን “ሄደህ ራስህን ለንጉሥ አክዓብ ግለጥለት፤ እኔም በምድር ላይ ዝናብን አዘንባለሁ” አለው።
ኤልያስም “የባዓልን ነቢያት ያዙ፤ አንድም ሰው እንዳያመልጥ!” ሲል አዘዘ፤ሕዝቡም በሙሉ ያዛቸው፤ ኤልያስም ወደ ቂሾን ወንዝ እየመራ ወስዶ በዚያ ሁሉንም ገደላቸው።
አንተ በሰማይ ሆነህ ጸሎታቸውን ስማ፤ የሚሄዱበትንም መልካም መንገድ በማሳየት የአገልጋዮችህን የእስራኤልን ኃጢአት ይቅር በል፤ ርስት አድርገህ ለሕዝብህ በሰጠሃቸው ምድር ዝናብ እንዲዘንብ አድርግ።