ከዚህ በኋላ የባዓል ነቢያት ወደ አምላካቸው ይጸልዩ፤ እኔም ወደ ጌታ እጸልያለሁ፤ እሳትን ወደ መሥዋዕቱ በመላክ መልስ የሚሰጥ እርሱ እውነተኛ አምላክ ነው።” ሕዝቡም ድምፁን ከፍ አድርጎ በዚህ ሐሳብ መስማማቱን ገለጠ።
1 ነገሥት 18:25 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚህ በኋላ ኤልያስ የበዓልን ነቢያት “እናንተ ብዙ ስለ ሆናችሁ በመጀመሪያ አንዱን ኰርማ መርጣችሁ በማረድ ወደ አምላካችሁ ጸልዩ፤ ነገር ግን እንጨቱን በእሳት አታቀጣጥሉ” አላቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኤልያስም ለበኣል ነቢያት፣ “እናንተ ብዙ ስለ ሆናችሁ በመጀመሪያ አንዱን ወይፈን መርጣችሁ አዘጋጁ፤ የአምላካችሁን ስም ጥሩ፤ ነገር ግን እሳት አታንድዱበት” አላቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ ኤልያስ የባዓልን ነቢያት “እናንተ ብዙ ስለ ሆናችሁ በመጀመሪያ አንዱን ኰርማ መርጣችሁ በማረድ ወደ አምላካችሁ ጸልዩ፤ ነገር ግን እንጨቱን በእሳት አታቀጣጥሉ” አላቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኤልያስም የበዓልን ነቢያት፥ “እናንተ ብዙዎች ናችሁና አስቀድማችሁ አንድ ወይፈን ምረጡና አዘጋጁ፤ የአምላካችሁንም ስም ጥሩ፤ በበታቹም እሳት አትጨምሩ” አላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኤልያስም የበኣልን ነቢያት “እናንተ ብዙዎች ናችሁና አስቀድማችሁ አንድ ወይፈን ምረጡና አዘጋጁ፤ የአምላካችሁንም ስም ጥሩ፤ በበታቹም እሳት አትጨምሩ፤” አላቸው። |
ከዚህ በኋላ የባዓል ነቢያት ወደ አምላካቸው ይጸልዩ፤ እኔም ወደ ጌታ እጸልያለሁ፤ እሳትን ወደ መሥዋዕቱ በመላክ መልስ የሚሰጥ እርሱ እውነተኛ አምላክ ነው።” ሕዝቡም ድምፁን ከፍ አድርጎ በዚህ ሐሳብ መስማማቱን ገለጠ።
እነርሱም የመጣላቸውን ኰርማ ወስደው ለመሥዋዕት አዘጋጅተው እስከ እኩለ ቀን ድረስ ወደ ባዓል ጸለዩ። “ባዓል ሆይ! እባክህ ስማን!” እያሉም ጮኹ። በሠሩትም መሠዊያ እየዘለሉ ዞሩ፤ ነገር ግን ምንም መልስ አላገኙም።