1 ነገሥት 17:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ ኤልያስ ወደ ሰራጵታ ሄደ፤ ወደ ከተማይቱም ቅጽር በር በደረሰ ጊዜ አንዲት ባሏ የሞተባት ሴት እንጨት ስትለቅም አይቶ “እባክሽ የምጠጣው ውሃ አምጪልኝ” አላት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ተነሥቶ ወደ ሰራፕታ ሄደ። ወደ ከተማዪቱ በር እንደ ደረሰም፣ አንዲት መበለት ጭራሮ ስትለቃቅም አገኛት፤ ጠርቶም፣ “የምጠጣው ውሃ በዕቃ ታመጪልኛለሽን?” ሲል ለመናት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ኤልያስ ወደ ሰራጵታ ሄደ፤ ወደ ከተማይቱም ቅጽር በር በደረሰ ጊዜ አንዲት ባልዋ የሞተባት ሴት እንጨት ስትለቅም አይቶ “እባክሽ የምጠጣው ውሃ አምጪልኝ” አላት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ተነሥቶም ወደ ሰራፕታ ሄደ፤ ወደ ከተማዪቱም በር በደረሰ ጊዜ አንዲት መበለት በዚያ እንጨት ትለቅም ነበር፤ ኤልያስም ጠርቶ፥ “የምጠጣው ጥቂት ውኃ በጽዋ ታመጭልኝ ዘንድ እለምንሻለሁ” አላት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ተነሥቶም ወደ ሰራፕታ ሄደ፤ ወደ ከተማይቱም በር በደረሰ ጊዜ አንዲት ባልቴት በዚያ እንጨት ትለቅም ነበር፤ እርሱም ጠርቶ “የምጠጣው ጥቂት ውሃ በጽዋ ታመጭልኝ ዘንድ እለምንሻለሁ፤” አላት። |
በድንጋይ ተወግረው ሞቱ፤ በመጋዝ ተሰነጠቁ፤ በሰይፍ ተገድለው ሞቱ፤ ሁሉን እያጡ መከራን እየተቀበሉ፥ እየተጨነቁ፥ የበግና የፍየል ሌጦ ለብሰው ዞሩ።