አኪጦፌልም ምክሩን እንዳልተከተሉት ባየ ጊዜ፥ አህያውን ጭኖ ቤቱ ወደሚገኝበት ወደ መኖሪያ ከተማው ሄደ፤ ቤቱንም አስተካክሎ በገዛ እጁ ታነቀ፤ ከሞተ በኋላ በአባቱም መቃብር ተቀበረ።
1 ነገሥት 16:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዚምሪ ከተማይቱ እንደ ተያዘች ባየ ጊዜ በቤተ መንግሥቱ ውስጠኛ ክፍል ወዳለው ምሽግ ውስጥ ገብቶ በቤተ መንግሥቱ ላይ እሳት ለቀቀበት፤ እርሱም በእሳት ነበልባል ተቃጥሎ ሞተ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዘምሪ ከተማዪቱ መያዟን ሲያይ፣ ቤተ መንግሥቱ ውስጥ ወዳለው ግንብ ገብቶ በቤተ መንግሥቱ ላይ እሳት ለቀቀበትና በዚሁ ሞተ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዚምሪ ከተማይቱ እንደ ተያዘች ባየ ጊዜ በቤተ መንግሥቱ ውስጠኛ ክፍል ወዳለው ምሽግ ውስጥ ገብቶ በቤተ መንግሥቱ ላይ እሳት ለቀቀበት፤ እርሱም በእሳት ነበልባል ተቃጥሎ ሞተ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዘምሪም ከተማዪቱ እንደ ተያዘች ባየ ጊዜ ወደ ንጉሡ ቤት ግንብ ውስጥ ገባ፤ የንጉሡንም ቤት በራሱ ላይ በእሳት አቃጠለ፤ ሞተም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዘምሪም ከተማይቱ እንደ ተያዘች ባየ ጊዜ ወደ ንጉሡ ቤት ግንብ ውስጥ ገባ፤ የንጉሡንም ቤት በራሱ ላይ በእሳት አቃጠለ፤ |
አኪጦፌልም ምክሩን እንዳልተከተሉት ባየ ጊዜ፥ አህያውን ጭኖ ቤቱ ወደሚገኝበት ወደ መኖሪያ ከተማው ሄደ፤ ቤቱንም አስተካክሎ በገዛ እጁ ታነቀ፤ ከሞተ በኋላ በአባቱም መቃብር ተቀበረ።
ከፈቃሕያ ሠራዊት መካከል ፈቁሔ ተብሎ የሚጠራ የረማልያ ልጅ የሆነ አንድ የጦር መኰንን ከኀምሳ የገለዓድ ሰዎች ጋር ሆኖ ሤራ ጠነሰሰ፤ በሰማርያ በቤተ መንግሥቱ ውስጥ በሚገኘው ምሽግ ውስጥ ዘልቆ በመግባትም ፈቃሕያን ከአርጎብና ከሃርዬ ጋር ገድሎ በፈቃሕያ እግር ተተክቶ ነገሠ።
ወዲያውም ጋሻ ጃግሬውን ጠርቶ፥ “‘ሴት ገደለችው’ እንዳይሉ እባክህ ሰይፍህን መዘህ ግደለኝ” አለው። ስለዚህ አገልጋዩ ወጋው፤ እርሱም ሞተ።