1 ነገሥት 15:21 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ንጉሥ ባዕሻ የሆነውን ነገር ሁሉ በሰማ ጊዜ ራማን የመመሸጉ ሥራ እንዲቆም አድርጎ ወደ ቲርጻ ሄደ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ባኦስም ይህን በሰማ ጊዜ፣ ራማን መገንባቱን አቁሞ ወደ ቴርሳ ተመለሰ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጉሥ ባዕሻ የሆነውን ነገር ሁሉ በሰማ ጊዜ ራማን የመመሸጉ ሥራ እንዲቆም አድርጎ ወደ ቲርጻ ሄደ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ባኦስም ያን በሰማ ጊዜ ራማን መሥራት ትቶ ወደ ቴርሳ ተመለሰ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ባኦስም ያን በሰማ ጊዜ ራማን መሥራት ትቶ በቴርሳ ተቀመጠ። |
ባዕሻ ይሁዳን በመውረር ራማን ምሽግ አድርጎ መሥራት ጀመረ፤ ይህንንም ያደረገው ወደ ይሁዳ ማንም እንዳይገባና ከዚያም ማንም እንዳይወጣ ለመከልከል ነው።
በዚህ ዓይነት አሳ በይሁዳ በነገሠ በሠላሳ አንደኛው ዓመት ዖምሪ በእስራኤል ላይ ነግሦ ዐሥራ ሁለት ዓመት ገዛ፤ የመጀመሪያዎቹን ስድስት ዓመቶች የገዛውም መኖሪያውን በቲርጻ አድርጎ ነበር።