1 ነገሥት 15:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መኖሪያውንም በኢየሩሳሌም አድርጎ አርባ አንድ ዓመት ገዛ፤ አያቱም ማዕካ ተብላ የምትጠራ የአቤሴሎም ልጅ ነበረች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በኢየሩሳሌምም አርባ አንድ ዓመት ነገሠ፤ እናቱ መዓካ ትባላለች፤ እርሷም የአቤሴሎም ልጅ ነበረች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መኖሪያውንም በኢየሩሳሌም አድርጎ አርባ አንድ ዓመት ገዛ፤ አያቱም ማዕካ ተብላ የምትጠራ የአቤሴሎም ልጅ ነበረች። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በኢየሩሳሌምም አርባ አንድ ዓመት ነገሠ፤ እናቱም ሐና የተባለች የአቤሴሎም ልጅ ነበረች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በኢየሩሳሌምም አርባ አንድ ዓመት ነገሠ፤ እናቱም መዓካ የተባለች የአቤሴሎም ልጅ ነበረች። |
አያቱ ማዕካ አሼራ ተብላ የምትጠራውን የሴት አምላክ አጸያፊ ጣዖት ስለ ሠራች ከእቴጌነት ሻራት፤ የሠራችውንም ጣዖት ሰባብሮ በቄድሮን ሸለቆ ውስጥ በእሳት አቃጠለው።
ሦስት ዓመት በኢየሩሳሌም ነገሠ፤ የእናቱም ስም ሚካያ ነበረ፥ የገብዓ ሰው የኡርኤል ልጅ ነበረች። በአብያና በኢዮርብዓም መካከል ጦርነት ነበረ።