1 ነገሥት 14:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የኢዮርብዓም ሚስት ወደ ቲርጻ ተመልሳ ወደ ቤትዋ ደጃፍ እንደ ደረሰች ወዲያውኑ ልጁ ሞተ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የኢዮርብዓም ሚስትም ተነሥታ ወደ ቴርሳ ሄደች፤ የቤቱን መድረክ ወዲያው እንደ ተራመደች ልጁ ሞተ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የኢዮርብዓም ሚስት ወደ ቲርጻ ተመልሳ ወደ ቤትዋ ደጃፍ እንደ ደረሰች ወዲያውኑ ልጁ ሞተ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የኢዮርብዓምም ሚስት ተነሥታ ሄደች፤ ወደ ቴርሳም መጣች፤ ወደ ቤቱም መድረክ በገባች ጊዜ ልጁ ሞተ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የኢዮርብዓምም ሚስት ተነሥታ ሄደች፤ ወደ ቴርሳ መጣች፤ ወደ ቤቱም መድረክ በገባች ጊዜ ልጁ ሞተ። |
አሳ በይሁዳ በነገሠ በሦስተኛው ዓመት የአኪያ ልጅ ባዕሻ በመላው እስራኤል ላይ ነገሠ፤ መኖሪያውንም በቲርጻ በማድረግ ኻያ አራት ዓመት ገዛ።
አሳ በይሁዳ በነገሠ በሃያ ሰባተኛው ዓመት ዚምሪ በእስራኤል ላይ ነገሠ፤ መኖሪያውንም በቲርጻ አድርጎ በእስራኤል ላይ ሰባት ቀን ብቻ ነገሠ፤ በዚያን ጊዜ የእስራኤል ወታደሮች በፍልስጥኤም የምትገኘውን የጊበቶንን ከተማ ከበው ነበር።
በዚህ ዓይነት አሳ በይሁዳ በነገሠ በሠላሳ አንደኛው ዓመት ዖምሪ በእስራኤል ላይ ነግሦ ዐሥራ ሁለት ዓመት ገዛ፤ የመጀመሪያዎቹን ስድስት ዓመቶች የገዛውም መኖሪያውን በቲርጻ አድርጎ ነበር።