1 ነገሥት 11:32 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለአገልጋዬ ለዳዊትና ከሌላው የእስራኤል ምድር የራሴ ርስት እንድትሆን ለመረጥኳት ለኢየሩሳሌም ከተማ ስል ለሰሎሞን አንድ ነገድ አስቀርቼለታለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን ስለ ባሪያዬ ስለ ዳዊትና ከእስራኤል ነገዶች ሁሉ ስለ መረጥኋት ከተማ ስለ ኢየሩሳሌም ስል አንድ ነገድ ይቀርለታል፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለአገልጋዬ ለዳዊትና ከሌላው የእስራኤል ምድር የራሴ ርስት እንድትሆን ለመረጥኳት ለኢየሩሳሌም ከተማ ስል ለሰሎሞን አንድ ነገድ አስቀርቼለታለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለ ባሪያዬ ስለ ዳዊት ከእስራኤልም ሀገሮች ሁሉ ስለ መረጥኋት ከተማ ስለ ኢየሩሳሌም ግን ሁለት ነገድ ይቀሩለታል፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለ ባሪያዬ ስለ ዳዊት ከእስራኤልም ነገድ ስለ መረጥኋት ከተማ ስለ ኢየሩሳሌም ግን አንድ ነገድ ይቀርለታል፤ |
ከልጅህም ቢሆን መንግሥቱን በሙሉ አልወስድበትም፤ ለአገልጋዬ ለዳዊትና ለራሴ ርስት እንድትሆን ለመረጥኳት ለኢየሩሳሌም ከተማ ስል አንድ ነገድ እተውለታለሁ።”
የሰሎሞን ልጅ ሮብዓም በይሁዳ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው አርባ አንድ ዓመቱ ነበር፤ እርሱም መኖሪያውን ጌታ ከመላው የእስራኤል ግዛት መካከል ለስሙ መጠሪያ እንድትሆን በመረጣት ከተማ በኢየሩሳሌም አድርጎ ዐሥራ ሰባት ዓመት ገዛ፤ የሮብዓም እናት ናዕማ ተብላ የምትጠራ ዐሞናዊት ነበረች።
ይሁን እንጂ ከእርሱ በኋላ በኢየሩሳሌም እንዲነግሥና ኢየሩሳሌምንም በሰላም እንዲጠብቅ ጌታ አምላኩ ስለ ዳዊት ሲል ለአቢያ አንድ ወንድ ልጅ ሰጠው።