1 ዮሐንስ 4:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነርሱ ከዓለም ናቸው፤ ስለዚህ ከዓለም የሆነውን ይናገራሉ ዓለምም ይሰማቸዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነርሱ ከዓለም ናቸው፤ ስለዚህ የሚናገሩት እንደ ዓለም ነው፤ ዓለምም ይሰማቸዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሐሰተኞች ነቢያት የዓለም ናቸው፤ የሚናገሩትም የዓለምን ነገር ነው። ዓለምም እነርሱን ይሰማቸዋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነርሱ ከዓለም ናቸው፤ ስለዚህ ከዓለም የሆነውን ይናገራሉ ዓለሙም ይሰማቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነርሱ ከዓለም ናቸው፤ ስለዚህ ከዓለም የሆነውን ይናገራሉ ዓለሙም ይሰማቸዋል። |
የእስራኤልም አምላክ የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላልና፦ በመካከላችሁ ያሉት ነብዮቻችሁና ምዋርተኞቻችሁ አያታልሉአችሁ፥ እናንተም የምታልሙትን ሕልም አትስሙ።
ነቢያት በሐሰት ትንቢት ይናገራሉ፥ ካህናትም በእነዚህ እጅ ይገዛሉ፥ ሕዝቤም እንዲህ ያለውን ነገር ወድደዋል፤ በፍጻሜውስ ምን ታደርጋላችሁ?
በነፋስና በውሸት የሚሄድ፥ ሐሰትንም የሚናገር፥ “ስለ ወይን ጠጅና ስለሚያሰክር መጠጥ ስብከት እናገርልሃለሁ” የሚል ሰው ቢኖር፥ እርሱ የዚህ ሕዝብ ሰባኪ ይሆናል።
ሰዎች እውነተኛውን ትምህርት የማይታገሱበት፤ ይልቁንም ጆሮዎቻቸውን የሚኮረኩራቸውን ነገር በመሻት ለራሳቸው ምኞት የሚመቹ አስተማሪዎችን የሚሰበስቡበት ጊዜ ይመጣልና።
ታላቁም ዘንዶ ወደ ታች ተጣለ፤ ዓለሙንም ሁሉ የሚያስተው፥ ዲያብሎስና ሰይጣን የሚባለው ታላቁ ዘንዶ እርሱም የቀደመው እባብ ተጣለ፤ ወደ ምድር ተጣለ፤ መላእክቱም ከእርሱ ጋር ተጣሉ።