1 ዮሐንስ 3:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ትእዛዙን የሚጠብቅ ሁሉ በእርሱ ይኖራል እርሱም ይኖርበታል፤ በእኛ እንደሚኖር በዚህ እናውቃለን፥ ይኸውም በሰጠን በመንፈሱ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ትእዛዞቹንም የሚጠብቁ ሁሉ በርሱ ይኖራሉ፤ እርሱም በእነርሱ ይኖራል። በእኛ መኖሩን በዚህ፣ ይኸውም እርሱ በሰጠን መንፈስ እናውቃለን። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእግዚአብሔርን ትእዛዝ የሚፈጽሙ ሁሉ በእግዚአብሔር ይኖራሉ፤ እግዚአብሔርም በእነርሱ ይኖራል። እግዚአብሔር በእኛ መኖሩን የምናውቀው እርሱ በሰጠን መንፈስ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ትእዛዙንም የሚጠብቅ በእርሱ ይኖራል እርሱም ይኖርበታል፤ በዚህም በእኛ እንዲኖር ከሰጠን ከመንፈሱ እናውቃለን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ትእዛዙንም የሚጠብቅ በእርሱ ይኖራል እርሱም ይኖርበታል፤ በዚህም በእኛ እንዲኖር ከሰጠን ከመንፈሱ እናውቃለን። |
እርሱም ዓለም ሊቀበለው የማይቻለው የእውነት መንፈስ ነው፤ ምክንያቱም ዓለም ስለማያየውና ስለማያውቀው ነው። ነገር ግን በእናንተ ዘንድ ስለሚኖር፥ በውስጣችሁም ስለሚሆን እናንተ ታውቁታላችሁ።
ይህም ሁሉም አንድ እንዲሆኑ፥ አንተም፥ አባት ሆይ! በእኔ እንዳለህና እኔም በአንተ እንዳለሁ እነርሱ ደግሞ በእኛ አንድ እንዲሆኑ፥ አንተም እንደ ላክኸኝ ዓለም እንዲያምን ነው።
ወይስ ሰውነታችሁ፥ ከእግዚአብሔር የተቀበላችሁት፥ በውስጣችሁም የሚኖረው የመንፈስ ቅዱስ ቤተ መቅደስ መሆኑን አታውቁም? እናንተም የራሳችሁ አይደላችሁም።
የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ከጣዖት ጋር ምን ስምምነት አለው? እኛ እኮ የሕያው እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ነን፤ እግዚአብሔርም እንዲህ ሲል ተናግሯል፥ በእነርሱ እኖራለሁ፤ በመካከላቸውም እመላለሳለሁ፤ አምላካቸውም እሆናለሁ፤ እነርሱም ሕዝቤ ይሆናሉ።
ወዳጆች ሆይ፥ ፍቅር ከእግዚአብሔር ስለ ሆነ፥ እርስ በርሳችን እንዋደድ፤ የሚያፈቅር ሁሉ ከእግዚአብሔር የተወለደ ነው፥ እግዚአብሔርንም ያውቃል።