1 ዮሐንስ 2:26 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለሚያታልሉአችሁ ሰዎች ይህን ጽፌላችኋለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለሚያስቷችሁ ሰዎች ይህን ጽፌላችኋለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለሚያታልሉአችሁ ሰዎች ይህን ጻፍኩላችሁ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለሚያስቱአችሁ ሰዎች ይህን ጽፌላችኋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለሚያስቱአችሁ ሰዎች ይህን ጽፌላችኋለሁ። |
ራስን ማዋረድና የመላእክትን አምልኮ እየወደደ፥ ባየውም ራእይ ላይ በጽኑ እየተመረኮዘ፥ በሥጋዊም አእምሮ በከንቱ እየታበየ ማንም አይፍረድባችሁ፤
እንደ ክርስቶስ ትምህርት ሳይሆን እንደ ሰው ወግና እንደ መሠረታዊው የዓለም ረቂቅ መንፈስ በፍልስፍናና በከንቱ መታለል ማንም እንዳይማርካችሁ ተጠንቀቁ።
መንፈስ ግን በግልጥ እንዲህ ይላል በኋለኞች ዘመናት አንዳንዶች የሚያስቱ መናፍስትንና የአጋንንትን ትምህርት ትኩረት በመስጠት እምነትን ይክዳሉ፤