1 ቆሮንቶስ 7:37 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሳይናወጥ በልቡ የጸና ግን ምንም አስገዳጅ የለበትም፤ ፍላጎቱን ለመቆጣጠር ከቻለና እጮኛውንም በልቡ ይጠብቅ ዘንድ ቢጸና፥ መልካም አደረገ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን በዚህ ጕዳይ ልቡን አረጋግቶ፣ ሳይናወጥ፣ ራሱንም በመግዛት ድንግሊቱን ላለማግባት የወሰነ ሰው መልካም አድርጓል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን አንድ ሰው በልቡ ከጸና፥ አስገዳጅ ነገር ከሌለበት፥ ፍላጎቱን ለመቈጣጠር ከቻለና እጮኛውን ላለማግባት ከወሰነ መልካም አደረገ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በልቡ የቈረጠና ያላወላወለ ግን የወደደውን ሊያደርግ ይችላል፤ ግድም አይበሉት፤ ድንግልናውንም ይጠብቅ ዘንድ በልቡ ቢጸና መልካም አደረገ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሳይናወጥ በልቡ የጸና ግን ግድ የለበትም፥ የወደደውን እንዲያደርግ ተፈቅዶለታል፤ ድንግልናውንም በልቡ ይጠብቅ ዘንድ ቢጸና፥ መልካም አደረገ። |
ዳሩ ግን አንድ ሰው በእጮኛው ላይ መልካም አለማድረጉን ቢያስብ፥ እጮኛውም ዕድሜዋ ለጋብቻ ከደረሰ፥ ሊያገባም ከፈቀደ፥ የወደደውን ያድርግ፤ ኃጢአት የለበትም፤ ይጋቡ።
ኀላፊነት የተሰጣችሁን የእግዚአብሔርን መንጋ ጠብቁ፤ ይህም በግድ ሳይሆን እንደ እግዚአብሔር ፍላጎት በፈቃደኝነት፥ ለጥቅም በመስገብገብ ሳይሆን በጽኑ ፍላጎት ይሁን፤