1 ቆሮንቶስ 7:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የማያምን ግን ቢለይ ይለይ፤ ወንድም ቢሆን ወይም እኅት እንዲህ በሚመስል ነገር አይገዙም፤ እግዚአብሔር ግን በሰላም ጠርቶናል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን የማያምነው ወገን መለየት ከፈለገ ይለይ፤ አንድ ወንድም ወይም እኅት በዚህ ሁኔታ የታሰሩ አይደሉም፤ እግዚአብሔር የጠራን በሰላም እንድንኖር ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ክርስቲያን ያልሆነ ወገን መለየት ከፈለገ ይለይ፤ በዚህ ጊዜ ግን ክርስቲያን የሆነው ወገን ባልም ሆነ ሚስት በምንም ዐይነት ግዴታ አይያዝም። እግዚአብሔር የጠራን በሰላም እንድንኖር ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የማያምን ግን ቢፈታ ይፍታ፤ ወንድምና እኅት እግዚአብሔር ለሰላም ስለ ጠራቸው እንደዚህ ላለ ግብር አይገዙምና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የማያምን ግን ቢለይ ይለይ፤ ወንድም ቢሆን ወይም እኅት እንዲህ በሚመስል ነገር አይገዙም፤ እግዚአብሔር ግን በሰላም ጠርቶናል። |
በቀረውስ ወንድሞች ሆይ! ደኅና ሁኑ። ፍጹማን ሁኑ፤ ምክሬን ስሙ፤ በአንድ ልብ ሁኑ፤ በሰላም ኑሩ፤ የፍቅርና የሰላምም አምላክ ከእናንተ ጋር ይሆናል።