1 ቆሮንቶስ 6:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን እናንተ ትበድላላችሁ፤ ታታልሉማላችሁ፤ ያውም ወንድሞቻችሁን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እናንተ ግን ራሳችሁ ትበድላላችሁ፤ ታታልላላችሁም፤ ያውም እኮ ወንድሞቻችሁን። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እናንተ ግን ወንድሞቻችሁ በሆኑት ክርስቲያኖች ላይ እንኳ በደልና ማታለል ትፈጽማላችሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሁንም ቢሆን፥ እናንተ ዐመፀኞችና ቀማኞች ናችሁ፤ እንደዚህም ወንድሞቻችሁን ትበድላላችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን እናንተ ትበድላላችሁ ታታልሉማላችሁ፥ ያውም ወንድሞቻችሁን። |
ለፍርድ ወደ እናንተ እቀርባለሁ፤ በአስማተኞች፥ በዘማውያን፥ በሐሰት በሚምሉ፥ የሠራተኛውን ደመወዝ በሚያስቀሩ፥ መበለቲቱንና የሙት ልጅን በሚያስጨንቁ፥ ስደተኛውን በሚገፉ፥ እኔንም በማይፈሩ ላይ ፈጣን ምስክር እሆንባቸዋለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ።
አስቀድመን ደግሞ እንደ ነገርናችሁና እንደ መሰከርንላችሁ፥ ጌታ ስለዚህ ነገር ሁሉ የሚበቀል ነውና፥ ማንም በዚህ ነገር አይተላለፍ፤ ወንድሙንም አያታልል።