Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




1 ቆሮንቶስ 6:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 እናንተ ግን ወንድሞቻችሁ በሆኑት ክርስቲያኖች ላይ እንኳ በደልና ማታለል ትፈጽማላችሁ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 እናንተ ግን ራሳችሁ ትበድላላችሁ፤ ታታልላላችሁም፤ ያውም እኮ ወንድሞቻችሁን።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ነገር ግን እናንተ ትበድላላችሁ፤ ታታልሉማላችሁ፤ ያውም ወንድሞቻችሁን።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 አሁ​ንም ቢሆን፥ እና​ንተ ዐመ​ፀ​ኞ​ችና ቀማ​ኞች ናችሁ፤ እን​ደ​ዚ​ህም ወን​ድ​ሞ​ቻ​ች​ሁን ትበ​ድ​ላ​ላ​ችሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 ነገር ግን እናንተ ትበድላላችሁ ታታልሉማላችሁ፥ ያውም ወንድሞቻችሁን።

Ver Capítulo Copiar




1 ቆሮንቶስ 6:8
8 Referencias Cruzadas  

በዚህ ነገር ማንም ሰው አይተላለፍ፤ ሌላ አማኝን አይበድል፤ ከዚህ በፊት እንደ ነገርናችሁና እንዳስጠነቀቅናችሁ እነዚህን ነገሮች የሚያደርጉትን ጌታ ይቀጣቸዋል።


በእግዚአብሔር ዘንድ አድልዎ ስለሌለ ክፉ የሚሠራም ስለ ክፉ ሥራው ቅጣቱን ይቀበላል።


ይሁን እንጂ በእርሻችሁ ሲያጭዱ ለዋሉት ሠራተኞች ዋጋቸውን ስላልከፈላችሁ እነሆ፥ የተቃውሞ ጩኸታቸው ይሰማል፤ የመከር ሰብሳቢዎቹንም ጩኸት የሠራዊት ጌታ ሰምቶአል።


ትእዛዞችን ታውቃለህ፤ እነርሱም ‘አትግደል፤ አታመንዝር፤ አትስረቅ፤ በሐሰት አትመስክር፤ አታታል፤ አባትህንና እናትህን አክብር፤’ የተባሉት ናቸው።”


የሠራዊት አምላክ እንዲህ ይላል፦ “ለፍርድ ወደ እናንተ እቀርባለሁ፤ በአስማተኞች፥ በዘማውያን፥ በሐሰት መስካሪዎች፥ የቀን ሠራተኞችን ደመወዝ አታለው በሚያስቀሩ አሠሪዎች፥ ባሎቻቸው የሞቱባቸውን ሴቶች፥ እናትና አባት የሌላቸው ልጆችንና ስደተኞችን በሚጨቊኑና እኔን በማይፈሩ ሰዎች ላይ ፈጣን ፍርዴን አስተላልፋለሁ።


የእርሻ ቦታ ሲፈልጉ የሌላውን ቀምተው ይወስዳሉ፤ ቤትም ሲፈልጉ ነጥቀው ይወስዳሉ፤ የሰውን መብት ረግጠው ሀብቱን ይዘርፋሉ።


“በጐረቤትህ ላይ ግፍ አትሥራ፤ ወይም ንብረቱን አትቀማው፤ ቀጥረህ የምታሠራውን ሰው ደመወዝ ለአንድ ሌሊት እንኳ በአንተ ዘንድ አይደር።


የወይኑ አትክልት ባለቤትም ከሠራተኞቹ ለአንዱ እንዲህ ሲል መለሰለት፤ ‘ወዳጄ ሆይ! ምንም አልበደልኩህም፤ የተዋዋልነው በቀን አንድ ዲናር ልከፍልህ አይደለምን?


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios