1 ቆሮንቶስ 3:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እንደ ሆናችሁ የእግዚአብሔርም መንፈስ እንደሚኖርባችሁ አታውቁምን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም እናንተ ራሳችሁ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እንደ ሆናችሁ፣ የእግዚአብሔርም መንፈስ በውስጣችሁ እንደሚኖር አታውቁምን? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ መሆናችሁንና የእግዚአብሔር መንፈስ በውስጣችሁ መኖሩን አታውቁምን? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እናንተ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እንደ ሆናችሁ፥ የእግዚአብሔር መንፈስም በእናንተ ላይ አድሮ እንደሚኖር አታውቁምን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እንደ ሆናችሁ የእግዚአብሔርም መንፈስ እንዲኖርባችሁ አታውቁምን? |
እርሱም ዓለም ሊቀበለው የማይቻለው የእውነት መንፈስ ነው፤ ምክንያቱም ዓለም ስለማያየውና ስለማያውቀው ነው። ነገር ግን በእናንተ ዘንድ ስለሚኖር፥ በውስጣችሁም ስለሚሆን እናንተ ታውቁታላችሁ።
እራሳችሁን የመታዘዝ ባርያዎች አድርጋችሁ ለምታቀርቡለት፥ ለምትታዘዙት ለእርሱ ሞትን ለሚያመጣው ለኃጢአት ወይም ጽድቅን ለሚያመጣው ለመታዘዝ ባርያዎች እንደ ሆናችሁ አታውቁምን?
ነገር ግን ኢየሱስን ከሙታን ያስነሣው መንፈስ በእናንተ የሚኖር ከሆነ፥ ክርስቶስን ከሙታን ያስነሣው መንፈስ፥ በውስጣችሁ በሚኖረው በመንፈሱ አማካይነት፥ ለሟች አካላቶቻችሁ ሕይወትን ይሰጠዋል።
እናንተ ግን የእግዚአብሔር መንፈስ በእናንተ የሚኖር ከሆነ፥ በመንፈስ እንጂ በሥጋ አይደላችሁም። ነገር ግን ማንም የክርስቶስ መንፈስ ከሌለው፥ እርሱ የክርስቶስ አይደለም።
ማንም የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ቢያፈርስ እግዚአብሔር እርሱን ያፈርሰዋል፤ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ቅዱስ ነው፤ ይኼውም እናንተ ናችሁ።
ወይስ ሰውነታችሁ፥ ከእግዚአብሔር የተቀበላችሁት፥ በውስጣችሁም የሚኖረው የመንፈስ ቅዱስ ቤተ መቅደስ መሆኑን አታውቁም? እናንተም የራሳችሁ አይደላችሁም።
ወይስ ዐመፀኞች የእግዚአብሔርን መንግሥት እንደማይወርሱ አታውቁምን? አትሳሳቱ፤ ሴሰኞች ቢሆኑ ወይም ጣዖትን የሚያመልኩ ወይም አመንዝሮች ወይም ግብረ ሰዶም የሚፈጽሙ፥
በሩጫ መወዳደሪያ ስፍራ የሚሮጡት ሁሉ እንደሚሮጡ ነገር ግን አንዱ ብቻ ሽልማቱን ዋጋውን እንደሚቀበል አታውቁምን? ስለዚህ እናንተም እንድትቀበሉ ሩጡ።
የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ከጣዖት ጋር ምን ስምምነት አለው? እኛ እኮ የሕያው እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ነን፤ እግዚአብሔርም እንዲህ ሲል ተናግሯል፥ በእነርሱ እኖራለሁ፤ በመካከላቸውም እመላለሳለሁ፤ አምላካቸውም እሆናለሁ፤ እነርሱም ሕዝቤ ይሆናሉ።
ይህ ሳይሆን ቀርቶ ብዘገይ ግን፥ በዚህ በጻፍሁልህ ትእዛዝ የሕያው እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን፥ የእውነት ዓምድና መሠረት በሆነችው በእግዚአብሔር ማደሪያ ቤት መኖር እንዴት እንደሚገባ እንድታውቅ ነው።
አመንዝሮች ሆይ! ከዓለም ጋር ወዳጅ መሆን የእግዚአብሔር ጠላትነት መሆኑን አታውቁምን? ስለዚህ የዓለም ወዳጅ መሆን የሚፈልግ ሁሉ የእግዚአብሔር ጠላት ሆኖአል።
እናንተ ደግሞ እንደ ሕያዋን ድንጋዮች ሆናችሁ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ለእግዚአብሔር ደስ የሚያሰኝ መንፈሳዊ መሥዋዕትን ለማቅረብ፥ ቅዱሳን ካህናት እንድትሆኑ፥ መንፈሳዊ ቤት ለመሆን ተሠሩ።