1 ቆሮንቶስ 2:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔም በድካምና በፍርሃት በብዙ መንቀጥቀጥም በእናንተ ዘንድ ነበርሁ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወደ እናንተ የመጣሁት በድካምና በፍርሀት፣ እንዲሁም በብዙ መንቀጥቀጥ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ከእናንተ ጋር በነበርኩበት ጊዜ ደካማ ሆኜ በፍርሃትና በብዙ መንቀጥቀጥ ላይ ነበርኩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔም በድካምና በፍርሀት፥ በብዙ መንቀጥቀጥም መጣሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔም በድካምና በፍርሃት በብዙ መንቀጥቀጥም በእናንተ ዘንድ ነበርሁ፤ |
ነገር ግን በተቃወሙትና በተሳደቡ ጊዜ፥ ልብሱን እያራገፈ “ደማችሁ በራሳችሁ ነው፤ እኔ ንጹሕ ነኝ፤ ከእንግዲህ ወዲህ ወደ አሕዛብ እሄዳለሁ፤” አላቸው።
በድካም ተሰቅሎአል፤ ነገር ግን በእግዚአብሔር ኃይል በሕይወት ይኖራል። እኛ ደግሞ ከእርሱ ጋር ደካሞች ብንሆን፤ እናንተ ለማገልገል በእግዚአብሔር ኃይል ከእርሱ ጋር በሕይወት እንኖራለን።
ወደ መቄዶንያም በመጣን ጊዜ፥ በሁሉ ነገር መከራን ተቀበልን እንጂ ሰውነታችን ዕረፍት አልነበረውም፤ ከውጭ ጠብ ነበረ፤ ከውስጥ ደግሞ ፍርሃት ነበረብን።