1 ቆሮንቶስ 15:44 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አካላዊ ሰውነት ይዘራል፥ መንፈሳዊ አካል ይነሣል። አካላዊ ሰውነት አለ፤ መንፈሳዊ አካል ደግሞ አለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ፍጥረታዊ አካል ይዘራል፤ መንፈሳዊ አካል ይነሣል። ፍጥረታዊ አካል ካለ መንፈሳዊ አካል ደግሞ አለ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሥጋዊ አካል ሆኖ የተዘራው መንፈሳዊ አካል ሆኖ ይነሣል። ሥጋዊ አካል ካለ መንፈሳዊ አካልም አለ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሥጋዊ አካል ይዘራል፤ መንፈሳዊ አካል ይነሣል፤ ሥጋዊ አካል አለና መንፈሳዊ አካልም ደግሞ አለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ፍጥረታዊ አካል ይዘራል፥ መንፈሳዊ አካል ይነሣል። ፍጥረታዊ አካል ካለ መንፈሳዊ አካል ደግሞ አለ። |
በዚያው ከሳምንቱ የመጀመሪያው በሆነው ቀን፥ በመሸ ጊዜ፥ ደቀመዛሙርቱ ተሰብስበው በነበሩበት፥ አይሁድን ስለ ፈሩ ደጆቹ ተዘግተው ሳሉ፥ ኢየሱስ መጣ፤ በመካከላቸውም ቆሞ “ሰላም ለእናንተ ይሁን” አላቸው።
ከስምንት ቀን በኋላም ደቀመዛሙርቱ ደግመው በቤት ውስጥ ነበሩ፤ ቶማስም ከእነርሱ ጋር ነበረ። ደጆቹ ተዘግተው ሳሉ ኢየሱስ መጣ፤ በመካከላቸውም ቆሞ “ሰላም ለእናንተ ይሁን” አላቸው።
ፍጥረታዊ ሰው ግን የእግዚአብሔርን መንፈስ ነገር አይቀበለውም፤ ይህ ለእርሱ ሞኝነት ነው፥ ምክንያቱም በመንፈስ የሚመረመር ነውና፥ ሊያውቀው አይችልም።