1 ቆሮንቶስ 14:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንደዋሽንትና እንደ በገና ያሉ ሕይወት የሌላቸው የሙዚቃ መሣሪያዎች እንኳ የድምፃቸው ቃና ልዩነት ከሌለው ዜማቸውን እንዴት ማወቅ ይቻላል? አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንደ ዋሽንትና እንደ በገና ያሉ ሕይወት የሌላቸው ነገሮች እንኳ፣ የድምፃቸው ቃና ልዩነት ከሌለው የዋሽንት ወይም የበገና ድምፅ መሆኑን እንዴት ማወቅ ይቻላል? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንደ ዋሽንትና እንደ ክራር ያሉት ነፍስ የሌላቸው የሙዚቃ መሣሪያዎች እንኳ የተለየ የድምፅ ቅኝት ከሌላቸው የሚሰጡት የሙዚቃ ድምፅ ምን መሆኑ እንዴት ይታወቃል? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነፍስ የሌለው ድምፅ የሚሰጥ እንደ መሰንቆ፥ ወይም እንደ ክራር ያለ መሣሪያ በስልት ካልተመታ መሰንቆው ወይም ክራሩ የሚለውን ማን ያውቃል? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነፍስ የሌለበት ነገር እንኳ ዋሽንትም ክራርም ቢሆን ድምፅ ሲሰጥ የድምፁን ልዩነት ባይገልጥ በዋሽንት የሚነፋው ወይስ በክራር የሚመታው መዝሙር እንዴት ይታወቃል? |
በገበያ የሚቀመጡትን ልጆች ይመስላሉ፤ እርስ በርሳቸውም እየተጠራሩ እንዲህ የሚሉትን እንቢልታ ነፋንላችሁ፤ አላሸበሸባችሁምም፤ ሙሾ አወረድንላችሁ፤ አላለቀሳችሁምም።
እንግዲህ ወንድሞች ሆይ፤ ወደ እናንተ በምመጣበት ጊዜ በልሳኖች ብናገር፥ በመግለጥ፥ በእውቀት ወይም በትንቢት ወይም በትምህርት ካልነገርኩአችሁ ምን እጠቅማችሃለሁ?
ከዚያ በኋላ የፍልስጥኤማውያን ጦር ወዳለበት ወደ እግዚአብሔር ተራራ ወደ ጊብዓ ትሄዳለህ። ወደ ከተማዪቱ እንደ ደረስክም የነቢያት ጉባኤ በበገና፥ በከበሮ፥ በዋሽንትና በመሰንቆ ታጅበው ትንቢት እየተናገሩ ከማምለኪያው ኰረብታ ላይ ሲወርዱ ታገኛቸዋለህ።