Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ቆሮንቶስ 14:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 ነፍስ የሌ​ለው ድምፅ የሚ​ሰጥ እንደ መሰ​ንቆ፥ ወይም እንደ ክራር ያለ መሣ​ሪያ በስ​ልት ካል​ተ​መታ መሰ​ን​ቆው ወይም ክራሩ የሚ​ለ​ውን ማን ያው​ቃል?

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 እንደ ዋሽንትና እንደ በገና ያሉ ሕይወት የሌላቸው ነገሮች እንኳ፣ የድምፃቸው ቃና ልዩነት ከሌለው የዋሽንት ወይም የበገና ድምፅ መሆኑን እንዴት ማወቅ ይቻላል?

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 እንደዋሽንትና እንደ በገና ያሉ ሕይወት የሌላቸው የሙዚቃ መሣሪያዎች እንኳ የድምፃቸው ቃና ልዩነት ከሌለው ዜማቸውን እንዴት ማወቅ ይቻላል?

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 እንደ ዋሽንትና እንደ ክራር ያሉት ነፍስ የሌላቸው የሙዚቃ መሣሪያዎች እንኳ የተለየ የድምፅ ቅኝት ከሌላቸው የሚሰጡት የሙዚቃ ድምፅ ምን መሆኑ እንዴት ይታወቃል?

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 ነፍስ የሌለበት ነገር እንኳ ዋሽንትም ክራርም ቢሆን ድምፅ ሲሰጥ የድምፁን ልዩነት ባይገልጥ በዋሽንት የሚነፋው ወይስ በክራር የሚመታው መዝሙር እንዴት ይታወቃል?

Ver Capítulo Copiar




1 ቆሮንቶስ 14:7
7 Referencias Cruzadas  

‘እንቢልታ ነፋንላችሁ ዘፈንም አልዘፈናችሁም ሙሾ አወጣንላችሁ፤ ዋይ ዋይም አላላችሁም’ ይሉአቸዋል።


በገ​በያ ተቀ​ም​ጠው ባል​ን​ጀ​ሮ​ቻ​ቸ​ውን ጠር​ተው፥ “አቀ​ነ​ቀ​ን​ላ​ችሁ፥ አል​ዘ​ፈ​ና​ች​ሁ​ምም፤ ሙሾም አወ​ጣ​ን​ላ​ችሁ፥ አላ​ለ​ቀ​ሳ​ች​ሁ​ምም የሚ​ሉ​አ​ቸው ልጆ​ችን ይመ​ስ​ላሉ።


የሰ​ውን ሁሉ ቋንቋ ባውቅ፥ የመ​ላ​እ​ክ​ት​ንም ሁሉ ቋንቋ ባውቅ፥ ነገር ግን ፍቅር ከሌ​ለኝ እን​ደ​ሚ​ጮህ ነሐስ፥ ወይም እን​ደ​ሚ​መታ ከበሮ መሆኔ ነው።


አሁ​ንም ወን​ድ​ሞች ሆይ፥ ወደ እና​ንተ መጥቼ በማ​ታ​ው​ቁት ቋንቋ ባነ​ጋ​ግ​ራ​ችሁ፥ የጥ​በብ ነገ​ር​ንም ቢሆን፥ የት​ን​ቢ​ት​ንም ነገር ቢሆን፥ የማ​ስ​ተ​ማር ሥራ​ንም ቢሆን ገልጬ ካል​ነ​ገ​ር​ኋ​ችሁ የም​ጠ​ቅ​ማ​ችሁ ጥቅም ምን​ድን ነው?


መለ​ከት የሚ​ነ​ፋም በታ​ወ​ቀው ስልት ካል​ነፋ ለጦ​ር​ነት ማን ይዘ​ጋ​ጃል?


ከዚ​ያም በኋላ የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ጭፍራ ወዳ​ለ​በት ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ኮረ​ብታ ትመ​ጣ​ለህ፤ በዚ​ያም ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ዊው ናሴብ አለ፤ ወደ​ዚ​ያም ወደ ከተ​ማ​ዪቱ በደ​ረ​ስህ ጊዜ በገ​ናና ከበሮ፥ እም​ቢ​ል​ታና መሰ​ንቆ ይዘው ትን​ቢት እየ​ተ​ና​ገሩ ከኰ​ረ​ብ​ታው መስ​ገጃ የሚ​ወ​ርዱ የነ​ቢ​ያ​ትን ጉባኤ ታገ​ኛ​ለህ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos