1 ቆሮንቶስ 12:21 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዐይን እጅን “አታስፈልገኝም፤” ልትለው አትችልም፤ ወይም ራስ ደግሞ እግሮችን “አታስፈልጉኝም፤” ሊላቸው አይችልም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዐይን እጅን፣ “አታስፈልገኝም” ሊለው አይችልም፤ ራስም እግርን፣ “አታስፈልገኝም” ሊለው አይችልም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዐይን እጅን “አንተ አታስፈልገኝም!” ሊለው አይችልም፤ ራስም እግርን “አንተ አታስፈልገኝም!” ሊለው አይችልም፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዐይን እጅን፥ “አልፈልግሽም” ልትላት አትችልም፤ ራስም፥ “እግሮችን አልፈልጋችሁም” ልትላቸው አትችልም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዓይን እጅን፦ አታስፈልገኝም ልትለው አትችልም፥ ወይም ራስ ደግሞ እግሮችን፦ አታስፈልጉኝም ሊላቸው አይችልም። |