1 ቆሮንቶስ 10:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እያንዳንዱ የሌሎችንም ጥቅም ያስብ እንጂ የራሱን ጥቅም አይፈልግ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እያንዳንዱ ሰው የባልንጀራውን ጥቅም እንጂ የራሱን ብቻ አይፈልግ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እያንዳንዱ ሰው የሌሎችንም ጥቅም ያስብ እንጂ የራሱን ጥቅም ብቻ አይፈልግ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለባልንጀራችሁ እንጂ ለራሳችሁ አታድሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እያንዳንዱ የባልንጀራውን ጥቅም እንጂ አንድ ስንኳ የራሱን ጥቅም አይፈልግ። |
እነሆ፥ ወደ እናንተ ለመምጣት ስዘጋጅ ይህ ሦስተኛዬ ነው፤ ሸክም አልሆንባችሁም፤ እናንተን እንጂ ያላችሁን አልፈልግም። ወላጆች ለልጆች እንጂ ልጆች ለወላጆች ገንዘብ ሊያከማቹ አይገባቸውምና።