1 ዜና መዋዕል 9:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በየትውልዳቸውም ወንድሞቻቸው ዘጠኝ መቶ ኀምሳ ስድስት ነበሩ፤ እነዚህ ሰዎች ሁሉ የአባቶቻቸው ቤቶች አለቆች ነበሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በትውልድ ሐረግ መዝገቡ ላይ በተጻፈው መሠረት ከብንያም ነገድ የሕዝቡ ቍጥር ዘጠኝ መቶ ኀምሳ ስድስት ነበረ፤ እነዚህ ሁሉ ወንዶች የቤተ ሰብ አለቆች ነበሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከብንያም ነገድ በኢየሩሳሌም ለመኖር የሄዱት በአጠቃላይ ዘጠኝ መቶ ኀምሳ ስድስት ቤተሰቦች ነበሩ፤ ከዚህ በላይ የተጠቀሱትም ወንዶች ሁሉ የቤተሰብ አለቆች ነበሩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በየትውልዳቸውም ወንድሞቻቸው ዘጠኝ መቶ አምሳ ስድስት ነበሩ፤ እነዚህ ሰዎች ሁሉ የአባቶቻቸው ቤቶች አለቆች ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በየትውልዳቸውም ወንድሞቻቸው ዘጠኝ መቶ አምሳ ስድስት ነበሩ፤ እነዚህ ሰዎች ሁሉ የአባቶቻቸው ቤቶች አለቆች ነበሩ። |