1 ዜና መዋዕል 8:33 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኔር ቂስን ወለደ፤ ቂስም ሳኦልን ወለደ፤ ሳኦልም ዮናታንን፥ ሜልኪሳን፥ አሚናዳብን፥ አስባኣልን ወለደ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኔር ቂስን ወለደ፤ ቂስም ሳኦልን ወለደ፤ ሳኦልም ዮናታንን፣ ሜልኪሳን፣ አሚናዳብን፣ አስበኣልን ወለደ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኔር ቂስን ወለደ፤ ቂስ ንጉሥ ሳኦልን ወለደ፤ ሳኦልም ዮናታን፥ ማልኪሹዓ፥ አቢናዳብና ኤሽባዓል ተብለው የሚጠሩትን አራት ወንዶች ልጆችን ወለደ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኔር ቂስን ወለደ፤ ቂስም ሳኦልን ወለደ፤ ሳኦልም ዮናታንን፥ ሜልኪሳን፥ አሚናዳብን፥ አስበኣልን ወለደ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኔር ቂስን ወለደ፤ ቂስም ሳኦልን ወለደ፤ ሳኦልም ዮናታንን፥ ሜልኪሳን፥ አሚናዳብን፥ አስባኣልን ወለደ። |
ስለዚህም ዳዊት የራሱን ሰዎች አዘዘ፤ እነርሱንም ገደሏቸው፤ እጅና እግራቸውንም ቆርጠው በኬብሮን ካለው ኲሬ አጠገብ ሰቀሏቸው። ነገር ግን የኢያቡስቴን ራስ ወስደው ኬብሮን በሚገኘው በአበኔር መቃብር አጠገብ ቀበሩት።
ቂስም ከእስራኤል ልጆች መካከል በመልከ ቀናነት ተወዳዳሪ የማይገኝለት፥ ቁመቱም ከሌሎቹ ሁሉ ይልቅ ከትከሻው በላይ ዘለግ ያለ፥ ሳኦል የተባለ ወጣት ልጅ ነበረው።