1 ዜና መዋዕል 8:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ብንያምም በኩሩን ቤላን፥ ሁለተኛውንም አስቤልን፥ ሦስተኛውንም አሐራን፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ብንያም የበኵር ልጁን ቤላን፣ ሁለተኛ ልጁን አስቤልን፣ ሦስተኛ ልጁን አሐራን፣ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ብንያም አምስት ወንዶች ልጆችን ወለደ፤ እነርሱም በየዕድሜአቸው ተራ፥ ቤላዕ፥ አሽቤል፥ አሕራሕ፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ብንያምም በኵሩን ቤላን፥ ሁለተኛውንም አስቤልን፥ ሦስተኛውንም አሐራን፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ብንያምም በኵሩን ቤላን፥ ሁለተኛውንም አስቤልን፥ ሦስተኛውንም አሐራን፥ |
እነዚህ ሁሉ የአሴር ልጆች፥ የአባቶቻቸው ቤቶች አለቆች፥ የተመረጡ ጽኑዓን ኃያላን ሰዎች፥ የመኳንንቱ አለቆች ነበሩ። በትውልዳቸውም በጦርነት ላይ ለመዋጋት የተቈጠሩ ሀያ ስድስት ሺህ ሰዎች ነበሩ።