1 ዜና መዋዕል 7:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የኡላምም ልጅ ባዳን ነበረ፤ እነዚህ የምናሴ ልጅ የማኪር ልጅ የገለዓድ ልጆች ነበሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የኡላም ወንድ ልጅ፤ ባዳን፤ እነዚህ የምናሴ ልጅ፣ የማኪር ልጅ፣ የገለዓድ ወንዶች ልጆች ናቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኡላም ደግሞ ባዳን ተብሎ የሚጠራ አንድ ልጅ ወለደ፤ እነዚህ ሁሉ የምናሴ የልጅ ልጅ የማኪር ልጅ የገለዓድ ዘሮች ናቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የኡላምም ልጅ ባዳን ነበረ፤ እነዚህ የምናሴ ልጅ የማኪር ልጅ የገለዓድ ልጆች ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የኡላምም ልጅ ባዳን ነበረ፤ እነዚህ የምናሴ ልጅ የማኪር ልጅ የገለዓድ ልጆች ነበሩ። |