1 ዜና መዋዕል 7:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ማኪርም ከሑፊምና ከሳፊን ወገን ሚስት አገባ፤ የእኅትዋም ስም መዓካ ነበረ፤ የሁለተኛውም ስም ሰለጰአድ ነበረ፤ ለሰለጰዓድም ሴቶች ልጆች ነበሩት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ማኪርም ከሑፊምና ከሳፊም ወገኖች ሚስት አገባ። እኅቱም መዓካ ትባል ነበር። ሌላው ዘሩ ሰለጰዓድ ሲሆን፣ እርሱም ሴቶች ልጆች ብቻ ነበሩት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ማኪር፥ ሑፊምና ሺፊም አንዳንድ ሴት እንዲያገቡ አደረገ፤ ማኪር ማዕካ ተብላ የምትጠራ እኅት ነበረችው፤ ጸሎፍሐድ ተብሎ የሚጠራው የማኪር ሁለተኛ ልጅ ሴቶች ልጆችን ብቻ ወለደ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ማኪርም ከሑፊምና ከሳፊን ወገን ሚስት አገባ፤ የእኅትየዋም ስም መዓካ ነበረ፤ የሁለተኛውም ስም ሰለጰዓድ ነበረ፤ ለሰለጰዓድም ሴቶች ልጆች ነበሩት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ማኪርም ከሑፊምና ከሳፊን ወገን ሚስት አገባ፤ የእኅትዋም ስም መዓካ ነበረ፤ የሁለተኛውም ስም ሰለጰአድ ነበረ፤ ለሰለጰዓድም ሴቶች ልጆች ነበሩት። |
የኦፌርም ልጅ ሰለጰአድ ሴቶች ልጆች እንጂ ወንዶች ልጆች አልነበሩትም፤ የሰለጰዓድም የሴቶች ልጆቹ ስም ማህለህ፥ ኑዓ፥ ዔግላ፥ ሚልካ፥ ቲርጻ ነበረ።