1 ዜና መዋዕል 6:66 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከቀዓትም ልጆች ወገኖች ለአንዳንዶቹ ከኤፍሬም ነገድ ከተሞች ድርሻ ነበራቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለአንዳንድ የቀዓት ጐሣዎችም ከኤፍሬም ነገድ ድርሻ ላይ የሚኖሩበት ከተማ ተሰጣቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከቀዓት ጐሣ አንዳንድ ቤተሰቦች በኤፍሬም ግዛት ውስጥ ከተሞችና የግጦሽ ቦታዎች ተመድበውላቸው ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከቀዓትም ልጆች ወገኖች ለአንዳንዶቹ ከኤፍሬም ነገድ ከተሞች ድርሻ ነበራቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከቀዓትም ልጆች ወገኖች ለአንዳንዶቹ ከኤፍሬም ነገድ ከተሞች ድርሻ ነበራቸው። |
እነዚህም የመማፀኛ ከተሞች ለእነርሱ ተሰጣቸው፤ እነርሱም፦ በተራራማው በኤፍሬም አገር ያለችውን ሴኬምና መሰማሪያዋ፥ ደግሞም ጌዝርና መሰማሪያዋ፥
ከተሞቹም ለሮቤል ነገድ በምድረ በዳ በደልዳላ ስፍራ ያለ ቤጼር፥ ለጋድም ነገድ በገለዓድ ያለ ራሞት፥ ለምናሴም ነገድ በባሳን ያለ ጎላን ነበሩ።