1 ዜና መዋዕል 6:54 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ማደሪያዎቻቸውም በየሰፈራቸው በየዳርቻቸው እነዚህ ናቸው፤ አንደኛው ዕጣ የወጣው ለአሮን ልጆች ለቀዓት ወገኖች ነበረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም መኖሪያዎቻቸው እንዲሆኑ የተመደቡላቸው ቦታዎች እነዚህ ናቸው፦ የመጀመሪያው ዕጣ የእነርሱ ስለ ሆነ፣ ከቀዓት ጐሣ ለሆኑት ለአሮን ዘሮች የተመደቡላቸው መኖሪያዎች እነዚህ ነበሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለአሮን ልጆች የተመደቡት የሰፈራ ቦታዎች የሚከተሉት ናቸው፤ የመጀመሪያው ዕጣ ለቃሃት ወገን ስለ ወጣ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ማደሪያዎቻቸውም በየሰፈራቸው በየዳርቻቸው እነዚህ ናቸው፤ ለአሮን ልጆች ለቀዓት ወገኖች አንደኛው ዕጣ ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ማደሪያዎቻቸውም በየሰፈራቸው በየዳርቻቸው እነዚህ ናቸው፤ ለአሮን ልጆች ለቀዓት ወገኖች አንደኛው ዕጣ ነበረ። |
በቀዓት ውስጥም የእንበረማውያን ወገን፥ የይስዓራውያንም ወገን፥ የኬብሮናውያንም ወገን፥ የዑዝኤላውያንም ወገን ይካተቱ ነበር፤ የቀዓታውያን ወገኖች እነዚህ ናቸው።