የአሦር ንጉሠ ነገሥት ቲግላት ፐሌሴር ዒዮን፥ አቤልቤትማዕካ፥ ያኖሐ፥ ቄዴሽና ሐጾር ተብለው የሚጠሩትን ከተሞች፥ እንዲሁም የገለዓድን፥ የገሊላንና የንፍታሌምን ግዛቶች በመውረር ሕዝቡን ወደ አሦር ማርኮ የወሰደውም ይኸው ፋቁሔ በነገሠበት ዘመን ነበር።
1 ዜና መዋዕል 5:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የአሦር ንጉሥ ቴልጌል-ቴልፌልሶር የማረከው ልጁ ብኤራ፤ እርሱም የሮቤል ነገድ አለቃ ነበረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የአሦር ንጉሥ ቴልጌልቴልፌልሶር ማርኮ የወሰደው ልጁ ብኤራ የሮቤል ነገድ አለቃ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የአሦር ንጉሥ ቴልጌልቴልፌልሶር የማረከው ልጁ ብኤራ፤ እርሱ የሮቤል ነገድ አለቃ ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የአሦር ንጉሥ ቴልጌልቴልፌልሶር የማረከው ልጁ ብኤራ፤ እርሱ የሮቤል ነገድ አለቃ ነበረ። |
የአሦር ንጉሠ ነገሥት ቲግላት ፐሌሴር ዒዮን፥ አቤልቤትማዕካ፥ ያኖሐ፥ ቄዴሽና ሐጾር ተብለው የሚጠሩትን ከተሞች፥ እንዲሁም የገለዓድን፥ የገሊላንና የንፍታሌምን ግዛቶች በመውረር ሕዝቡን ወደ አሦር ማርኮ የወሰደውም ይኸው ፋቁሔ በነገሠበት ዘመን ነበር።
ከዚህም የተነሣ ንጉሥ አካዝ ወደ አሦር ንጉሠ ነገሥት ወደ ቲግላት ፐሌሴር “እኔ ለአንተ ታማኝ አገልጋይህ ነኝ፤ ስለዚህም ወደ እኔ መጥተህ አደጋ ከጣሉብኝ ከሶርያና ከእስራኤል ነገሥታት እጅ አድነኝ” የሚል ጥያቄ የያዙ መልእክተኞች ላከ።
የእስራኤልም አምላክ የአሦርን ንጉሥ የፎሐን መንፈስ፥ የአሦርንም ንጉሥ የቴልጌል-ቴልፌልሶርን መንፈስ አስነሣ፤ የሮቤልንና የጋድን ልጆች የምናሴንም ነገድ እኩሌታ አፈለሰ፥ እስከ ዛሬም ወዳሉበት ወደ አላሔና ወደ አቦር፥ ወደ ሃራና ወደ ጎዛን ወንዝ አመጣቸው።