የአባቶቻቸውም ቤቶች አለቆች እነዚህ ነበሩ፤ ዔፌር፥ ይሽዒ፥ ኤሊኤል፥ ዓዝርኤል፥ ኤርምያ፥ ሆዳይዋ፥ ኢየድኤል፤ እነርሱ ጽኑዓን ኃያላን የታወቁ ሰዎች የአባቶቻቸውም ቤቶች አለቆች ነበሩ።
1 ዜና መዋዕል 5:23 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የምናሴ የነገድ እኩሌታ ልጆች በምድሪቱ ተቀመጡ። ከባሳንም ጀምሮ እስከ በኣል-አርሞንዔምና እስከ ሳኔር እስከ አርሞንዔም ተራራ ድረስ በዙ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የምናሴ ነገድ እኩሌታ ሕዝብ ቍጥር ብዙ ነበረ፤ እነርሱም ከባሳን ጀምሮ እስከ በኣል አርሞንዔም ድረስ ባለው ምድር ሰፈሩ፤ ይህም እስከ ሳኔር አርሞንዔም ተራራ ድረስ ማለት ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በስተ ምሥራቅ ያለው የምናሴ ነገድ እኩሌታ በስተ ሰሜን እስከ ባዓልሔርሞን፤ እስከ ሠኒርና እስከ ሔርሞን ተራራ በሚደርሰው በባሳን ግዛት ውስጥ ይኖሩ ነበር፤ የሕዝባቸውም ቊጥሩ እየበዛ ሄደ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የምናሴም የነገድ እኩሌታ ልጆች፤ ከባሳን ጀምሮ እስከ በኣልአርሞንና እስከ ሳኔር እስከ አርሞንኤም ተራራ እስከ ሊባኖስ ድረስ ተቀመጡ፤ እነርሱም በዙ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የምናሴ የነገድ እኵሌታ ልጆች በምድሪቱ ተቀመጡ። ከባሳንም ጀምሮ እስከ በኣልአርሞንዔምና እስከ ሳኔር እስከ አርሞንዔም ተራራ ድረስ በዙ። |
የአባቶቻቸውም ቤቶች አለቆች እነዚህ ነበሩ፤ ዔፌር፥ ይሽዒ፥ ኤሊኤል፥ ዓዝርኤል፥ ኤርምያ፥ ሆዳይዋ፥ ኢየድኤል፤ እነርሱ ጽኑዓን ኃያላን የታወቁ ሰዎች የአባቶቻቸውም ቤቶች አለቆች ነበሩ።
ሙሽራዬ ሆይ፥ ከሊባኖስ ከእኔ ጋር ነዪ፥ ከሊባኖስ ከእኔ ጋር ነዪ፥ ከአማና ራስ ከሳኔርና ከኤርሞን ራስ፥ ከአንበሶች መኖሪያ ከነብሮችም ተራራ ተመልከች።
ለላሞች በኩር ግርማ ይሆናል፥ ቀንዶቹ አንድ ቀንድ እንዳለው ናቸው፥ በእነርሱ እስከ ምድር ዳርቻ ያሉትን አሕዛብ ሁሉ ይወጋል፥ የኤፍሬም እልፍ አእላፋት፥ የምናሴም አእላፋት እነርሱ ናቸው።”