1 ዜና መዋዕል 4:40 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የለመለመም እጅግም ያማረ መሰማሪያ አገኙ፥ ምድሪቱም ሰፊ ጸጥታም ያለላትና ሰላም የሰፈነባት ነበረች፤ በቀድሞም ጊዜ በዚያ ተቀምጠው የነበሩ ከካም ወገን ነበሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያም ለምለምና ያማረ የግጦሽ ቦታ አገኙ፤ ምድሪቱም ሰፊ፣ ሰላምና ጸጥታ የሰፈነባት ነበረች። በቀድሞ ዘመን በዚህ ምድር ይኖሩ የነበሩት አንዳንድ የካም ዘሮች ናቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያም ጸጥታና ሰላም በሰፈነበት ገላጣማ አገር ለም የሆነ የግጦሽ ቦታ በብዛት አገኙ፤ ቀደም ሲል በዚያ ይኖሩ የነበሩ ሕዝቦች ከካም ዘሮች ነበሩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ብዙና እጅግ ያማረ መሰማርያም አገኙ፤ ምድሪቱም በፊታቸው ሰፊና ጸጥተኛ ሰላም ያላትም ነበረች፤ በቀድሞም ጊዜ በዚያ ተቀምጠው የነበሩ ከካም ወገን ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የለመለመችም እጅግም ያማረች መሰማርያ አገኙ፤ ምድሪቱም ሰፊና ጸጥተኛ ሰላም ያላትም ነበረች፤ በቀድሞም ጊዜ በዚያ ተቀምጠው የነበሩ ከካም ወገን ነበሩ። |