1 ዜና መዋዕል 3:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነዚህ ደግሞ በኢየሩሳሌም ተወለዱለት፤ ከዓሚኤል ልጅ ከቤርሳቤህ አራት ልጆች እነርሱም ሳምዓ፥ ሶባብ፥ ናታን፥ ሰሎሞን፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በኢየሩሳሌም የተወለዱለትም ልጆች እነዚህ ነበሩ፤ ሳሙስ፣ ሶባብ፣ ናታን፣ ሰሎሞን፤ እነዚህ አራት ወንዶች ልጆች ከዓሚኤል ልጅ ከቤርሳቤህ የተወለዱ ናቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያም ብዙ ወንዶች ልጆችን ወለደ። የዓሚኤል ልጅ ቤርሳቤህ ሺምዓ፥ ሾባብ፥ ናታንና ሰሎሞን ተብለው የሚጠሩ አራት ወንዶች ልጆችን ወለደችለት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነዚህ ደግሞ በኢየሩሳሌም ተወለዱለት፤ ከዓሚል ልጅ ከቤርሳቤህ ስማዕ፥ ሶባብ፥ ናታን፥ ሰሎሞን፥ አራት፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነዚህ ደግሞ በኢየሩሳሌም ተወለዱለት፤ ከዓሚኤል ልጅ ከቤርሳቤህ፥ ሳሙስ፥ ሶባብ፥ ናታን፥ ሰሎሞን፥ አራት። |
ንጉሡም “አቢሻግን በሚስትነት እንድድርለት ብቻ ለምን ትጠይቂኛለሽ? መንግሥቴንም ጭምር እንድለቅለት ለምን አልጠየቅሽኝም? እርሱ እኮ ታላቅ ወንድሜ ነው፤ ለምን ለካህኑ አብያታርና ለኢዮአብም ልዩ አስተያየት እንዳደርግላቸው አትጠይቂላቸውም!” አላት።