1 ዜና መዋዕል 3:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በኬብሮንም ለዳዊት የተለወዱለት ልጆች እነዚህ ናቸው። በኩሩ አምኖን ከኢይዝራኤላዊቱ ከአኪናሆም፥ ሁለተኛውም ዳንኤል ከቀርሜሎሳዊቱ ከአቢግያ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዳዊት በኬብሮን ሳለ የተወለዱለት ወንዶች ልጆች እነዚህ ነበሩ፤ የበኵር ልጁ አምኖን ከኢይዝራኤላዊቷ ከአኪናሆም፣ ሁለተኛው ዳንኤል፣ ከቀርሜሎሳዊቷ ከአቢግያ፣ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዳዊት በኬብሮን ሳለ የወለዳቸው ወንዶች ልጆች ስም እንደ ዕድሜአቸው ቅደም ተከተል እንደሚከተለው ነው፦ በኲሩ የኢይዝራኤል ተወላጅ ከሆነችው ከአሒኖዓም የተወለደው አምኖን፥ ሁለተኛው የቀርሜሎስ ተወላጅ ከሆነችው ከአቢጌል የተወለደው ዳንኤል፥ ሦስተኛው የገሹር ንጉሥ የታልማይ ልጅ ከሆነችው ከማዕካ የተወለደው አቤሴሎም፥ አራተኛው ከሐጊት የተወለደው አዶንያስ፥ አምስተኛው ከአቢጣል የተወለደው ሸፋጥያ፥ ስድስተኛው ከዔግላ የተወለደው ዩትረዓም፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በኬብሮን ለዳዊት የተወለዱለት ልጆች እነዚህ ናቸው። በኵሩ አምኖን ከኢይዝራኤላዊቱ ከአኪናሆም፥ ሁለተኛውም ዶለህያ ከቀርሜሎሳዊቱ ከአቢግያ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በኬብሮንም ለዳዊት የተለወዱለት ልጆች እነዚህ ናቸው። በኵሩ አምኖን ከኢይዝራኤላዊቱ ከአኪናሆም፥ ሁለተኛውም ዳንኤል ከቀርሜሎሳዊቱ ከአቢግያ፥ |
የአቤሴሎምም አገልጋዮች በአምኖን ላይ አቤሴሎም ያዘዛቸውን ፈጸሙ። ከዚያም የንጉሡ ልጆች በሙሉ ተነሥተው በየበቅሎዎቻቸው ላይ ተቀምጠው ሸሹ።
ዳዊት ከኬብሮን ከመጣ በኋላ፥ ከበፊቶቹ በተጨማሪ በኢየሩሳሌም ተጨማሪ ዕቁባቶችን አስቀመጠ፤ ሚስቶችም አገባ፤ ብዙ ወንዶችና ሴቶች ልጆችም ተወለዱለት።
በያቤጽም የተቀመጡ የጸሐፊዎች ወገኖች፤ ቲርዓውያን፥ ሺምዓታውያን፥ ሡካታውያን ነበሩ፤ እነዚህ ከሬካብ ቤት አባት ከሐማት የወጡ ቄናውያን ናቸው።
ዳዊትና ሰዎቹ በጋት በአኪሽ ዘንድ ተቀመጡ፤ እያንዳንዱ ሰው ከቤተሰቡ ጋር ነበረ፤ ዳዊትም ከሁለቱ ሚስቶቹ ጋር፥ ከኢይዝራኤላዊቷ ከአሒኖዓም እና የናባል ሚስት ከነበረችው ከቀርሜሎሳዊቷ አቢጌል ጋር ነበር።