በንጉሡም ቤተ መዛግብት ላይ የዓዲኤል ልጅ ዓዛሞት ሹም ነበረ፤ በአገሩም በከተሞቹም በመንደሮቹም በግንቦቹም ባሉ ቤተ መዛግብት ላይ የዖዝያ ልጅ ዮናታን ሹም ነበረ፤
1 ዜና መዋዕል 27:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጽሩያ ልጅ ኢዮአብ መቁጠር ጀመረ፥ ነገር ግን አልፈጸመም፤ ስለዚህም በእስራኤል ላይ ቁጣ ወረደ፥ ቁጥራቸውም በንጉሡ በዳዊት መዝገብ አልተጻፈም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የጽሩያ ልጅ ኢዮአብ መቍጠር ጀመረ፤ ሆኖም አልፈጸመውም፤ መቈጠራቸው በእስራኤል ላይ ቍጣ ስላመጣ፣ የተቈጠረውም በንጉሡ ዳዊት መዝገብ አልገባም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የጸሩያ ልጅ ኢዮአብ የሕዝብ ቈጠራ ማድረግ ጀምሮ ሳይጨርስ ቀርቶ ነበር፤ በዚህ በሕዝብ ቈጠራ ምክንያት እግዚአብሔር የእስራኤልን ሕዝብ ቀጥቶ ስለ ነበር የመጨረሻው ቊጥር በንጉሥ ዳዊት መንግሥት የታሪክ መዝገብ ውስጥ አልተመዘገበም ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሶርህያ ልጅ ኢዮአብም መቍጠር ጀመረ፤ ነገር ግን አልፈጸመም፤ ስለዚህ ነገር በእስራኤል ላይ ቍጣ ሆነ፤ ቍጥራቸውም በንጉሡ በዳዊት የታሪክ መጽሐፍ አልተጻፈም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የጽሩያ ልጅ ኢዮአብ መቍጠር ጀመረ፥ ነገር ግን አልፈጸመም፤ ስለዚህም በእስራኤል ላይ ቍጣ ሆነ፥ ቍጥራቸውም በንጉሡ በዳዊት መዝገብ አልተጻፈም። |
በንጉሡም ቤተ መዛግብት ላይ የዓዲኤል ልጅ ዓዛሞት ሹም ነበረ፤ በአገሩም በከተሞቹም በመንደሮቹም በግንቦቹም ባሉ ቤተ መዛግብት ላይ የዖዝያ ልጅ ዮናታን ሹም ነበረ፤