1 ዜና መዋዕል 27:22 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዳን ላይ የይሮሐም ልጅ ዓዛርኤል አለቃ ነበረ፤ እነዚህ የእስራኤል ነገዶች አለቆች ነበሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዳን ነገድ ላይ የተሾመው፣ የይሮሐም ልጅ ዓዛርኤል። እንግዲህ የእስራኤል ነገድ አለቆች እነዚህ ነበሩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዳን ወገንም ላይ የኢዮራም ልጅ ዓዛርኤል፤ እነዚህ የእስራኤል ነገዶች አለቆች ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዳን ላይ የይሮሐም ልጅ ዓዛርኤል፤ እነዚህ የእስራኤል ነገዶች አለቆች ነበሩ። |
ዳዊትም የእስራኤልን አለቆች ሁሉ፥ የነገዶቹንም አለቆች፥ ንጉሡንም በክፍል የሚያገለግሉትን የሠራዊቱ አለቆች፥ ሻለቆቹንም፥ የመቶ አለቆቹንም፥ በንጉሥና በልጆቹ ሀብትና ግዛት ላይ የተሾሙትን፥ ጃንደረቦችንም፥ ጽኑዓን ኃያላኑንም ሁሉ ወደ ኢየሩሳሌም ሰበሰበ።