ኢዮአብም አለ፦ “ጌታ ሕዝቡን በአሁኑ ላይ መቶ እጥፍ ይጨምር፤ ጌታዬ ንጉሥ ሆይ! ሁሉ የጌታዬ ባርያዎች አይደሉምን? ይህን ነገር ጌታዬ ለምን ይሻል? በእስራኤል ላይ በደል ስለምን ያመጣል?”
1 ዜና መዋዕል 21:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን የንጉሡ ቃል በኢዮአብ ላይ አሸነፈ፤ ኢዮአብም ወጥቶ በእስራኤል ሁሉ ላይ ተዘዋወረ፥ ወደ ኢየሩሳሌምም ተመለሰ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይሁን እንጂ የንጉሡ ቃል ኢዮአብን አሸነፈው፤ ስለዚህ ኢዮአብ ወጣ፤ በመላው እስራኤል ከተዘዋወረ በኋላ፣ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሰ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጉሡ ግን ትእዛዙን እንዲፈጽም ኢዮአብን አስገደደው፤ ከዚህ በኋላ ኢዮአብ ከንጉሡ ፊት ወጣ፤ ሕዝቡንም ለመቊጠር በአገሪቱ በሙሉ ተዘዋውሮ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሰ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን የንጉሡ ቃል በኢዮአብ ላይ አሸነፈ፤ ኢዮአብም ወጥቶ በእስራኤል ሁሉ ላይ ተዘዋወረ፤ ወደ ኢየሩሳሌምም መጣ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን የንጉሡ ቃል በኢዮአብ ላይ አሸነፈ፤ ኢዮአብም ወጥቶ በእስራኤል ሁሉ ላይ ተዘዋወረ፤ ወደ ኢየሩሳሌምም መጣ። |
ኢዮአብም አለ፦ “ጌታ ሕዝቡን በአሁኑ ላይ መቶ እጥፍ ይጨምር፤ ጌታዬ ንጉሥ ሆይ! ሁሉ የጌታዬ ባርያዎች አይደሉምን? ይህን ነገር ጌታዬ ለምን ይሻል? በእስራኤል ላይ በደል ስለምን ያመጣል?”
ኢዮአብም የቈጠራቸውን የሕዝቡን ድምር ለዳዊት ሰጠ፤ ከእስራኤልም ሁሉ አንድ ሚሊዮን አንድ መቶ ሺህ ሰይፍ የሚመዝዙ ሰዎችን አገኘ፤ ከይሁዳም አራት መቶ ሰባ ሺህ ሰይፍ የሚመዝዙ ሰዎችን አገኘ።