አንተ፦ አብራምን ባለ ጠጋ አደረግሁት እንዳትል፥ ብላቴኖቹ ከበሉት በቀር ከእኔ ጋር ከሄዱትም ድርሻ በቀር፥ ፈትልም ቢሆን የጫማ ማዘቢያም ቢሆን፥ ለአንተ ከሆነው ሁሉ እንዳልወስድ፥ አውናን ኤስኮልም መምሬም እነርሱ ድርሻቸውን ይውሰዱ።
1 ዜና መዋዕል 21:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ንጉሡም ዳዊት ኦርናን፦ “አይደለም፥ ነገር ግን የአንተ የሆነውን ለጌታ አምጥቼ የሚቃጠል መሥዋዕት አድርጌ በከንቱ አላቀርብምና በሙሉ ዋጋ እገዛዋለሁ” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ንጉሥ ዳዊት ግን ኦርናን “እንዲህ አይደረግም፤ ሙሉውን ዋጋ እኔ እከፍላለሁ፤ የአንተ የሆነውን ለእግዚአብሔር ለማቅረብ አልፈልግም፤ ዋጋ ያልከፈልሁበትንም የሚቃጠል መሥዋዕት አድርጌ አላቀርብም” ሲል መለሰለት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጉሥ ዳዊት ግን “ይህስ አይሆንም፤ ሙሉውን ዋጋ እከፍልሃለሁ፤ የአንተ ንብረት የሆነውን፥ እኔ ምንም ዋጋ ያልከፈልኩበትን ነገር ለእግዚአብሔር መሥዋዕት አድርጌ ማቅረብ አልፈልግም” ሲል መለሰለት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ንጉሡም ዳዊት ኦርናን፥ “አይደለም፥ ነገር ግን ለአንተ ያለውን ለእግዚአብሔር አምጥቼ የሚቃጠል መሥዋዕት በከንቱ አላቀርብምና በተገቢው ዋጋ እገዛዋለሁ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ንጉሡም ዳዊት ኦርናን “አይደለም፤ ነገር ግን ለአንተ ያለውን ለእግዚአብሔር አምጥቼ የሚቃጠል መሥዋዕት በከንቱ አላቀርብምና በሙሉ ዋጋ እገዛዋለሁ፤” አለው። |
አንተ፦ አብራምን ባለ ጠጋ አደረግሁት እንዳትል፥ ብላቴኖቹ ከበሉት በቀር ከእኔ ጋር ከሄዱትም ድርሻ በቀር፥ ፈትልም ቢሆን የጫማ ማዘቢያም ቢሆን፥ ለአንተ ከሆነው ሁሉ እንዳልወስድ፥ አውናን ኤስኮልም መምሬም እነርሱ ድርሻቸውን ይውሰዱ።
የአገሩ ሰዎችም እየሰሙ ለኤፍሮን እንዲህ ሲል ተናገረ፦ “ፈቃድህ ከሆነ፥ አድምጠኝ፤ የእርሻውን ዋጋ እሰጥሃለሁ፥ አንተም ከእኔ ተቀበለኝና የሚስቴን አስክሬን እዚያ ወስጄ ልቅበር” አለው።
በእርሻው ዳር ያለውን ድርብ ክፍል ያላትን ዋሻውን ይስጠኝ፥ ይህ ስፍራ የመቃብር ቦታ እንዲሆንልኝ በእናንተ ፊት ሙሉ ዋጋ ከፍዬ እንዲሰጠኝ አድርጉልኝ።”
ንጉሡ ግን ኦርናን፥ “መክፈል ያለብኝን ዋጋ ላንተ ከፍዬ እንጂ እንዲሁማ አይሆንም፤ ለጌታም ለአምላኬ የሚቃጠል መሥዋዕት ያለ ዋጋ አላቀርብም” አለው። ስለዚህም ዳዊት ዐውድማውንና በሬዎቹን በአምሳ ሰቅል ብር ገዛ፤
ኦርናም ዳዊትን እንዲህ አለው፦ “ለአንተ ውሰደው፥ ጌታዬ ንጉሡም ደስ የሚያሰኘውን ያድርግ፤ እነሆ፥ ለሚቃጠለው መሥዋዕት በሬዎቹን፥ ለማገዶም የአውድማውን መውቅያ፥ ለእህልም ቁርባን ስንዴውን እሰጥሃለሁ፤ ሁሉን እሰጣለሁ።”