1 ዜና መዋዕል 21:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ሂድ፥ ለዳዊት፦ ‘ጌታ እንዲህ ይላል፦ ሦስቱን ነገሮች በፊትህ አኖራለሁ፤ በአንተ ላይ እንዳደርግብህ ከእነርሱ አንዱን ምረጥ’ ብለህ ንገረው” ብሎ ተናገረው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ሂድና ዳዊትን እንዲህ ብለው ንገረው፤ ‘እግዚአብሔር የሚለው ይህን ነው፤ እነሆ፣ ሦስት ምርጫ ሰጥቼሃለሁ፤ በአንተ ላይ አደርግብህ ዘንድ አንዱን ምረጥ።’ ” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ሄደህ ዳዊትን ‘እነሆ ሦስት ምርጫ ሰጥቼሃለሁ፤ እኔም አንተ የምትመርጠውን አደርጋለሁ’ ይላል” ብለህ ንገረው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ሂድ፥ ለዳዊት፦ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ሦስቱን ነገሮች በፊትህ አኖራለሁ፤ አደርግብህ ዘንድ ከእነርሱ አንዱን ምረጥ ብለህ ንገረው።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) “ሂድ፤ ለዳዊት እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ‘ሦስቱን ነገሮች በፊትህ አኖራለሁ፤ አደርግብህ ዘንድ ከእነርሱ አንዱን ምረጥ፤’ ብለህ ንገረው፤” ብሎ ተናገረው። |
ጌታም ሙሴንና አሮንን እንዲህ አላቸው፦ “በእስራኤል ልጆች ፊት ቅድስናዬን ለማሳየት በእኔ አላመናችሁምና ስለዚህ ወደ ሰጠኋቸው ምድር ይህን ጉባኤ ይዛችሁ አትገቡም።”
ጌታንም ማገልገል ክፉ መስሎ ቢታያችሁ፥ አባቶቻችሁ በወንዝ ማዶ ሳሉ ያገለገሉአቸውን አማልክት ወይም በምድራቸው የተቀመጣችሁባቸውን የአሞራውያንን አማልክት ታገለግሉ እንደሆነ፥ የምታገለግሉትን ዛሬ ምረጡ። እኔና ቤቴ ግን ጌታን እናገለግላለን።”