ከራፋይም ዘሮች አንዱ የሆነ ይሽቢበኖብ የተባለ ዳዊትን ለመግደል አሰበ። የናስ ጦሩ ሦስት መቶ ሰቅል የሚመዝንና አዲስ ሰይፍ የታጠቀ ሰው ነበረ።
1 ዜና መዋዕል 20:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ደግሞ በጌት ላይ ጦርነት ተደርጎ ነበረ፤ ከዚያም በእጁና በእግሩ ስድስት ስድስት ባጠቃላይ ሀያ አራት ጣቶች ያሉት አንድ ረጅም ሰው ነበረ፤ እርሱም ደግሞ ከራፋይም የተወለደ ነበረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ደግሞም ጋት ላይ በተደረገ ሌላ ጦርነት፣ በእጆቹና በእግሮቹ ላይ ስድስት ስድስት ጣት በድምሩ ሃያ አራት ጣት የነበሩት አንድ ግዙፍ ሰው ነበረ፤ ይህም እንደዚሁ ከራፋይም ዘር ነበረ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሌላም ጦርነት በጋት ተደረገ፤ በዚያም ጦርነት በእያንዳንዱ እጅና በእያንዳንዱ እግር ላይ ስድስት ስድስት በጠቅላላ ኻያ አራት ጣቶች የነበሩት አንድ ረጅም ሰው ነበር፤ እርሱም ኀያላን ከሆኑት ከራፋይም ዘር ነበር፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ደግሞ በጌት ላይ ሰልፍ ሆነ ፤ በዚያም በእጁና በእግሩ ስድስት ስድስት ጣቶች በጠቅላላው ሃያ አራት ጣቶች ያሉት አንድ ረዥም ሰው ነበረ፤ እርሱም ደግሞ ከኀያላን የተወለደ ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ደግሞ በጌት ላይ ሰልፍ ነበረ፤ ከዚያም በእጁና በእግሩ ስድስት ስድስት ባጠቃላይ ሃያ አራት ጣቶች ያሉት አንድ ረጅም ሰው ነበረ፤ እርሱም ደግሞ ከራፋይም የተወለደ ነበረ። |
ከራፋይም ዘሮች አንዱ የሆነ ይሽቢበኖብ የተባለ ዳዊትን ለመግደል አሰበ። የናስ ጦሩ ሦስት መቶ ሰቅል የሚመዝንና አዲስ ሰይፍ የታጠቀ ሰው ነበረ።
እንደገና ጌት ላይ በተደረገው ጦርነት በእያንዳንዱ እጁና በእያንዳንዱ እግሩ ስድስት ስድስት ጣቶች ባጠቃላይ ሃያ አራት ጣቶች የነበሩት አንድ ግዙፍ ሰው ነበረ፤ እርሱም ደግሞ ከራፋይም ዘር ነበረ።
ዳግመኛም ከፍልስጥኤማውያን ጋር ጦርነት ተደርጎ ነበር፤ የያዒርም ልጅ ኤልያናን የጦሩ እጀታ እንደ ሸማኔ መጠቅለያ የነበረውን የጌት ሰው የጎልያድን ወንድም ለሕሚን ገደለ።