አምላክ ሆይ! ይህ በፊትህ ጥቂት የሆነ ነገር ነበረ፤ አቤቱ አምላክ ሆይ! ስለ ባርያህ ቤት ደግሞ ስለ ወደ ፊቱ ሩቅ ዘመን ተናገርህ፤ እንደ አንድ ባለ ማዕረግ ሰው ተመለከትኸኝ።
1 ዜና መዋዕል 17:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንተ ባርያህን ታውቀዋለህና ለባርያህ ስለተደረገው ክብር ዳዊት ጨምሮ የሚለው ምን ነገር አለው? አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ባሪያህን ስላከበርኸው፣ ዳዊት ከዚህ በላይ ምን ሊልህ ይችላል? ባሪያህን አንተ ታውቀዋለህ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንግዲህ ለአንተ ከዚህ በላይ ምን መናገር እችላለሁ? አንተ እኔን ታውቀኛለህ፤ ይሁን እንጂ ለእኔ ክብር ሰጥተኸኛል፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንተ ባሪያህን ታውቀዋለህና ለባሪያህ ስለ ተደረገው ክብር ዳዊት ጨምሮ የሚለው ምንድን ነው? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አንተ ባሪያህን ታውቀዋለህና ለባሪያህ ስለ ተደረገው ክብር ዳዊት ጨምሮ የሚለው ምንድር ነው? |
አምላክ ሆይ! ይህ በፊትህ ጥቂት የሆነ ነገር ነበረ፤ አቤቱ አምላክ ሆይ! ስለ ባርያህ ቤት ደግሞ ስለ ወደ ፊቱ ሩቅ ዘመን ተናገርህ፤ እንደ አንድ ባለ ማዕረግ ሰው ተመለከትኸኝ።
ለሦስተኛ ጊዜም “የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ! ትወደኛለህን?” አለው። ለሦስተኛ ጊዜ “ትወደኛለህን?” ስላለው ጴጥሮስ አዘነና “ጌታ ሆይ! አንተ ሁሉን ታውቃለህ፤ እንደምወድህ አንተ ታውቃለህ” አለው። ኢየሱስም “በጎቼን አሰማራ።
ልጆችዋንም በሞት እገድላቸዋለሁ፤ አብያተ ክርስቲያናትም ሁሉ፥ ኩላሊትንና ልብን የምመረምር እኔ እንደሆንሁ ያውቃሉ፤ ለእያንዳንዳችሁም እንደ ሥራችሁ እሰጣችኋለሁ።
ጌታ ግን ሳሙኤልን፥ “መልኩን ወይም ቁመቱን አትይ፤ እኔ ንቄዋለሁና። ጌታ የሚያየው፥ ሰው እንደሚያየው አይደለም። ሰው የውጭውን ገጽታ ያያል፤ ጌታ ግን ልብን ያያል” አለው።
ስለዚህ የእስራኤል አምላክ ጌታ እንዲህ ይላል፦ ‘በእውነት ቤትህ፥ የአባትህም ቤት ለዘለዓለም በፊቴ እንዲኖር ተናግሬአለሁ፤’ አሁን ግን ጌታ እንዲህ ይላል፦ ‘ያከበሩኝን አከብራለሁና፥ የናቁኝም ይናቃሉና ይህ ከእኔ ይራቅ።