ዳዊት ከኬብሮን ከመጣ በኋላ፥ ከበፊቶቹ በተጨማሪ በኢየሩሳሌም ተጨማሪ ዕቁባቶችን አስቀመጠ፤ ሚስቶችም አገባ፤ ብዙ ወንዶችና ሴቶች ልጆችም ተወለዱለት።
1 ዜና መዋዕል 14:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዳዊትም በኢየሩሳሌም ሚስቶችን ጨምሮ አገባ ሌሎችንም ወንዶችና ሴቶችን ልጆች ወለደ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዳዊት በኢየሩሳሌም ተጨማሪ ሚስቶች አገባ፤ ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ልጆችም ወለደ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያም በኢየሩሳሌም ዳዊት ብዙ ሚስቶችን አገባ፤ ብዙ ወንዶችንና ሴቶች ልጆችንም ወለደ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳዊትም በኢየሩሳሌም ሌሎች ሚስቶችን ጨምሮ አገባ፤ ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ልጆችም ተወለዱለት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳዊትም በኢየሩሳሌም ሚስቶችን ጨምሮ ሌሎችን ወንዶችና ሴቶችን ልጆች ወለደ። |
ዳዊት ከኬብሮን ከመጣ በኋላ፥ ከበፊቶቹ በተጨማሪ በኢየሩሳሌም ተጨማሪ ዕቁባቶችን አስቀመጠ፤ ሚስቶችም አገባ፤ ብዙ ወንዶችና ሴቶች ልጆችም ተወለዱለት።
በሕይወትህ፥ አንተም ከፀሐይ በታች በምትደክምበት ድካም ይህ እድል ፈንታህ ነውና ከንቱ በሆነ በሕይወትህ ዘመን ሁሉ፥ ከፀሐይ በታች በሰጠህ፥ በከንቱ ዘመንህ ሁሉ፥ ከምትወድዳት ሚስትህ ጋር ደስ ይበልህ።
እናንተም፦ ለምን ይህ ሆነ? ትላላችሁ። ምክንያቱም ሚስትህን አታልለሃታልና ጌታ በአንተና በልጅነት ሚስትህ መካከል ምስክር ስለ ሆነ ነው፤ እርሷም ጓደኛህና የቃል ኪዳን ሚስትህ ነበረች።