ከዚህ በኋላ ዳዊት፥ “ከይሁዳ ከተሞች ወደ አንዲቱ ልውጣን?” ብሎ ጌታን ጠየቀ። ጌታም፥ “አዎን ውጣ” አለው። ዳዊትም፥ “ወደ የትኛዪቱ ልሂድ?” ሲል ጠየቀ። እርሱም፥ “ወደ ኬብሮን” ብሎ መለሰለት።
1 ዜና መዋዕል 14:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዳዊትም፦ “ወደ ፍልስጥኤማውያን ልውጣን? በእጄስ አሳልፈህ ትሰጣቸዋለህን?” ብሎ እግዚአብሔርን ጠየቀ። ጌታም፦ “በእጅህ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁና ውጣ” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህም ዳዊት፣ “በፍልስጥኤማውያን ላይ ወጥቼ ልምታቸውን? በእጄስ አሳልፈህ ትሰጣቸዋለህን?” ሲል እግዚአብሔርን ጠየቀ። እግዚአብሔርም፣ “አዎን ውጣ! በእጅህ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ” ብሎ መለሰለት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዳዊትም “በፍልስጥኤማውያን ላይ ጦርነት ልክፈትን? በእነርሱስ ላይ ድልን ታጐናጽፈኛለህን?” ሲል እግዚአብሔርን ጠየቀ። እግዚአብሔርም “አዎ፥ አደጋ ጣልባቸው! እኔም ድልን አጐናጽፍሃለሁ!” አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳዊትም፥ “ወደ ፍልስጥኤማውያን ልውጣን? በእጄስ አሳልፈህ ትሰጣቸዋለህን?” ብሎ እግዚአብሔርን ጠየቀ። እግዚአብሔርም፥ “በእጅህ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁና ውጣ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳዊትም “ወደ ፍልስጥኤማውያን ልውጣን? በእጄስ አሳልፈህ ትሰጣቸዋለህን?” ብሎ እግዚአብሔርን ጠየቀ። እግዚአብሔርም “በእጅህ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁና ውጣ፤” አለው። |
ከዚህ በኋላ ዳዊት፥ “ከይሁዳ ከተሞች ወደ አንዲቱ ልውጣን?” ብሎ ጌታን ጠየቀ። ጌታም፥ “አዎን ውጣ” አለው። ዳዊትም፥ “ወደ የትኛዪቱ ልሂድ?” ሲል ጠየቀ። እርሱም፥ “ወደ ኬብሮን” ብሎ መለሰለት።
ስለዚህም ዳዊት ጌታን፥ “ፍልስጥኤማውያንን ወጥቼ ልውጋቸው? በእጄስ አሳልፈህ ትሰጠኛለህ?” ሲል ጠየቀ። ጌታም፥ “ሂድ፤ በእርግጥ ፍልስጥኤማውያንን በእጅህ አሳልፌ እሰጥሃለሁ” አለው።
ስለዚህ አክዓብ አራት መቶ የሚሆኑትን ነቢያቱን ጠርቶ “ወደ ራሞት ሄጄ አደጋ ልጣልባት ወይስ ልተው?” ሲል ጠየቃቸው። እነርሱም “ሄደህ አደጋ ጣልባት፤ ጌታም ድልን ያቀዳጅሃል” ሲሉ መለሱለት።
ወደ በኣል-ፐራሲምም ወጡ፥ በዚያም ዳዊት ድል ነሣቸው። ዳዊትም፦ “ግድቡን አፍርሶ እንደሚወጣ ጎርፍ እግዚአብሔር ጠላቶቼን በእጄ አፈረሳቸው” አለ። ስለዚህም የዚያን ስፍራ ስም በኣል-ፐራሲም ብለው ጠሩት።
ዳዊትም እንደገና እግዚአብሔርን ጠየቀ፤ እግዚአብሔርም እንዲህ አለው፦ “ከእነርሱ ዞረህ በሾላው ዛፍ ፊት ለፊት ግጠማቸው እንጂ ወደ እነርሱ አትውጣ።
ዳዊትም፥ “ይህን ወራሪ ሠራዊት ልከተለውን? እደርስባቸዋለሁን?” ሲል ጌታን ጠየቀ። ጌታም፥ “በእርግጥ ትደርስባቸዋለህ፤ ምርኮውንም ትመልሳለህ፤ ተከተላቸው!” ሲል መለሰለት።