1 ዜና መዋዕል 13:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወደ ኪዶንም አውድማ በደረሱ ጊዜ በሬዎቹ ይፋንኑ ነበርና ታቦቱን ሊይዝ ዖዛ እጁን ዘረጋ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወደ ኪዶን ዐውድማ በደረሱ ጊዜ በሬዎቹ አደናቅፏቸው ስለ ነበር፣ ዖዛ ታቦቱን ለመደገፍ እጁን ዘረጋ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወደ ኪዶንም አውድማ በደረሱ ጊዜ ሠረገላውን የሚጐትቱት በሬዎች ሲፋንኑ አደናቀፋቸው፤ ዑዛም እጆቹን ዘርግቶ የቃል ኪዳኑን ታቦት በመደገፍ ያዘ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ አውድማ ዳርም በደረሱ ጊዜ ላሞቹ ሰረገላውን ሲስቡ የእግዚአብሔር ታቦት ዘንበል ብላለችና ታቦቷን ሊይዝ ዖዛ እጁን ዘረጋ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ ኪዶንም አውድማ በደረሱ ጊዜ በሬዎቹ ይፋንኑ ነበርና ታቦቱን ሊይዝ ዖዛ እጁን ዘረጋ። |