የእግዚአብሔርንም ታቦት በአዲስ ሠረገላ ላይ አኑረው፥ በኰረብታ ላይ ካሚገኘው ከአቢናዳብ ቤት አውጥተው አመጡ፤ ሠረገላውን ይነዱ የነበሩትም የአቢናዳብ ልጆች ዖዛና አሒዮ ነበሩ፤
1 ዜና መዋዕል 13:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእግዚአብሔርንም ታቦት በአዲስ ሠረገላ ላይ ጫኑት፥ ከአሚናዳብም ቤት አመጡት፤ ዖዛና አሒዮም ሠረገላውን ይነዱ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእግዚአብሔርንም ታቦት ከአሚናዳብ ቤት በአዲስ ሠረገላ ላይ አድርገው አመጡት፤ ሠረገላውን ይነዱ የነበሩትም ዖዛና አሒዮ ነበሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የቃል ኪዳኑን ታቦት ከአቢናዳብ ቤት አውጥተው በአዲስ ሠረገላ ላይ ጫኑት፤ ዑዛና አሕዮም ሠረገላውን ይነዱ ነበር፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእግዚአብሔርንም ታቦት ከአሚናዳብ ቤት በተገኘ በአዲስ ሰረገላ ላይ አኖሩአት። ዖዛና ወንድሞቹም ሰረገላውን ይነዱ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእግዚአብሔርንም ታቦት በአዲስ ሠረገላ ላይ ጫኑት፤ ከአሚናዳብም ቤት አመጡት፤ ዖዛና አሒዮም ሠረገላውን ይነዱ ነበር። |
የእግዚአብሔርንም ታቦት በአዲስ ሠረገላ ላይ አኑረው፥ በኰረብታ ላይ ካሚገኘው ከአቢናዳብ ቤት አውጥተው አመጡ፤ ሠረገላውን ይነዱ የነበሩትም የአቢናዳብ ልጆች ዖዛና አሒዮ ነበሩ፤
በዚያን ጊዜም ዳዊት እንዲህ አለ፦ “የእግዚአብሔርን ታቦት እንዲሸከሙ፥ ለዘለዓለሙም እንዲያገለግሉት ጌታ ከመረጣቸው ከሌዋውያን በቀር ማንም የጌታን ታቦት ሊሸከም አይገባውም።”
አሮንና ልጆቹ መቅደሱንና የመቅደሱን ዕቃዎች ሁሉ መሸፈናቸውን በጨረሱ ጊዜ፥ ሰፈሩም ለመጓዝ ሲነሣ፥ የቀዓት ልጆች ሊሸከሙት ከዚያም በኋላ ይመጣሉ፤ እንዳይሞቱ ግን ንዋየ ቅድሳቱን አይንኩ። የቀዓት ልጆች የሚሸከሙአቸው የመገናኛው ድንኳን ዕቃዎች እነዚህ ናቸው።
ስለዚህ አዲስ ሠረገላና ቀንበር ያልተጫነባቸው ሁለት የሚያጠቡ ላሞች አዘጋጁ። ላሞቹን በሠረገላው ጥመዷቸው፤ እንቦሶቻቸውን ግን ወደ ቤት መልሷቸው።