1 ዜና መዋዕል 13:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእግዚአብሔርም ታቦት በአቢ-ዳራ ቤተሰብ ዘንድ በቤቱ ውስጥ ሦስት ወር ተቀመጠ፤ ጌታም የአቢ-ዳራን ቤትና ያለውን ሁሉ ባረከ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእግዚአብሔርንም ታቦት በአቢዳራ ቤት ከቤተ ሰቡ ጋራ ሦስት ወር ተቀመጠ፤ እግዚአብሔርም ቤተ ሰቡንና ያለውንም ሁሉ ባረከ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ታቦቱም በዚያ ሦስት ወር ቈየ፤ እግዚአብሔርም የዖቤድኤዶምን ቤተሰብና የእርሱ የሆነውን ነገር ሁሉ ባረከ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእግዚአብሔርም ታቦት በጌት ሰው በአቢዳራ ቤት ውስጥ ሦስት ወር ተቀመጠች፤ እግዚአብሔርም አቢዳራንና ቤተ ሰቡን ሁሉ ባረከ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእግዚአብሔርም ታቦት በአቢዳራ ቤተ ሰብ ዘንድ በቤቱ ውስጥ ሦስት ወር ተቀመጠ፤ እግዚአብሔርም የአቢዳራን ቤትና ያለውን ሁሉ ባረከ። |
ዮሴፍ በጲጥፋራ ቤትና ባለው ሀብት ሁሉ ላይ ከተሾመበት ጊዜ ጀምሮ ጌታ የግብፃዊውን ቤት ባረከ፥ የጌታም በረከት በግቢም በውጭም ባለው የጲጥፋራ ሀብት ንብረት ሁሉ ላይ ሆነ።
ስለዚህ ዳዊት የጌታን ታቦት አብሮት እንዲሆን ወደ ዳዊት ከተማ ይዞት ለመሄድ አልፈለገም፤ በዚህ ፈንታ አቅጣጫ ለውጦ የጌት ሰው ወደ ሆነው ወደ ዖቤድ ኤዶም ቤት ወሰደው።