Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ዜና መዋዕል 13:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ዳዊትም ታቦቱን ወደ ጌት ሰው ወደ አቢ-ዳራ ቤት ወሰደው እንጂ ወደ እርሱ ወደ ዳዊት ከተማ አላመጣውም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ስለዚህ ታቦቱን ወደ ዳዊት ከተማ በመውሰድ ፈንታ የጋት ሰው ወደ ሆነው ወደ አቢዳራ ቤት ወሰደው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ስለዚህም ዳዊት ታቦቱን ወደ ኢየሩሳሌም በመውሰድ ፈንታ የጋት ከተማ ነዋሪ በሆነው፥ ዖቤድኤዶም ተብሎ በሚጠራው ሰው ቤት ተወው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 ዳዊ​ትም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታቦት ወደ ጌት ሰው ወደ አቢ​ዳራ ቤት አሳ​ለ​ፋት እንጂ ወደ እርሱ ወደ ዳዊት ከተማ አላ​መ​ጣ​ትም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 ዳዊትም ታቦቱን ወደ ጌት ሰው ወደ አቢዳራ ቤት አሳለፈው እንጂ ወደ እርሱ ወደ ዳዊት ከተማ አላመጣውም።

Ver Capítulo Copiar




1 ዜና መዋዕል 13:13
9 Referencias Cruzadas  

የበኤሮት ሕዝብ ወደ ጊታይም በመሸሽ እስከ ዛሬም በመጻተኝነት እዚያው ይኖራሉ።


ዳዊት እንደገና ከእስራኤል የተመረጡትን ሠላሳ ሺህ ሰዎች ሰበሰበ።


በዚያም ቀን ዳዊት፦ “የእግዚአብሔርን ታቦት ወደ እኔ እንዴት አመጣለሁ?” ብሎ እግዚአብሔርን ፈራ።


ከእነርሱም ጋር በሁለተኛው ደረጃ ያሉትን ወንድሞቻቸውን ዘካርያስን፥ ቤንን፥ ያዝኤልን፥ ሰሚራሞትን፥ ይሒኤልን፥ ዑኒን፥ ኤልያብን፥ በናያስን፥ መዕሤያን፥ መቲትያን፥ ኤሊፍሌሁን፥ ሚቅኔያን፥ ደጁንም የሚጠብቁትን ዖቤድ-ኤዶምንና ይዒኤልን ሾሙ።


ዳዊትም፥ የእስራኤልም ሽማግሌዎች፥ የሻለቆችም የጌታን የቃል ኪዳኑን ታቦት ከዖቤድ-ኤዶም ቤት በደስታ ለማምጣት ሄዱ።


አለቃው አሳፍ ነበረ፤ ከእርሱም ቀጥሎ መሰንቆና በገና ይጫወቱ የነበሩት ዘካርያስ፥ ይዒኤል፥ ሰሚራሞት፥ ይሒኤል፥ መቲትያ፥ ኤልያብ፥ በናያስ፥ ዖቤድ-ኤዶም፥ ይዒኤል ነበሩ፤ አሳፍም የጸናጽልን ድምፅ ያሰማ ነበረ።


ዖቤድ-ኤዶም ልጆች ነበሩት፤ እነርሱም በኩሩ ሸማያ፥ ሁለተኛው ዮዛባት፥ ሦስተኛው ኢዮአስ፥ አራተኛው ሣካር፥ አምስተኛው ናትናኤል፥


እነርሱም ልጆቻቸውም ወንድሞቻቸውም ለማገልገል ኃያላን የነበሩ የዖቤድ-ኤዶም ልጆች ስልሳ ሁለት ነበሩ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos