1 ዜና መዋዕል 12:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አለቃው ዔጼር፥ ሁለተኛው አብድዩ፥ ሦስተኛው ኤልያብ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእነዚህም አለቃ ዔጼር ነበረ፤ ሁለተኛው አዛዥ አብድዩ፣ ሦስተኛው ኤልያብ፣ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእነርሱም ስም በሚከተለው ሁኔታ በየማዕርጋቸው በቅደም ተከተል ተራ ተዘርዝሮአል፦ ዔዜር፥ አብድዩ ኤሊአብ፥ ሚሽማና፥ ኤርምያስ፥ ዓታይ፥ ኤሊኤል፥ ዮሐናን፥ ኤልዛባድ፥ ኤርምያስ ማክባናይ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አለቃው አዝር፥ ሁለተኛው አብድያ፥ ሦስተኛው ኤልያብ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አለቃው ዔጼር፥ ሁለተኛው አብድዩ፥ ሦስተኛው ኤልያብ፥ |
ዳዊትም በምድረ በዳ ውስጥ ባለችው በአምባይቱ ሳለ ከጋድ ወገን የሆኑ እነዚህ በጋሻና በጦር ስልታቸው የተካኑ፥ ጽኑዓን ኃያላን፥ ተዋጊዎች፥ ወደ እርሱ መጡ፤ ፊታቸውም እንደ አንበሳ ፊት ነበረ፥ በተራራም ላይ እንደሚዘልል ሚዳቋ ፈጣኖች ነበሩ።