ከእርሱ ዘሮች ሰባት ወንዶች ልጆች ይሰጠን፤ እኛም ከጌታ በተመረጠው በሳኦል አገር በጊብዓ በጌታ ፊት እንስቀላቸው” ብለው መለሱለት። ስለዚህ ንጉሡ፥ “እሺ! እሰጣችኋለሁ” አለ።
1 ዜና መዋዕል 12:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አለቃቸው አሒዔዝር ነበረ፥ ከእርሱም በኋላ ኢዮአስ፥ ሁለቱም የጊብዓዊው የሸማዓ ልጆች ነበሩ፤ እንዲሁም ይዝኤል፥ ፋሌጥ፥ የዓዝሞት ልጆች ነበሩ፤ በራኪያ፥ ዓናቶታዊው ኢዩ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም አለቃቸው አሒዔዝር ነበረ፤ ከርሱም በኋላ ኢዮአስ ነበረ፤ ሁለቱም የጊብዓዊው የሸማዓ ልጆች ነበሩ፤ የዓዝሞት ልጆች ይዝኤልና ፋሌጥ፣ በራኪያ፣ ዓናቶታዊው ኢዩ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱ የጊብዓ ተወላጅ የሆነው የኢሸማዓ ልጆች በሆኑት በአሒዔዜርና በዮአሽ አመራር ሥር ነበሩ። የወታደሮቹም ስም ዝርዝር እንደሚከተለው ነው፦ የዓዝማዌት ልጆች ይዚኤልና ፔሌጥ፥ የዐናቶት ተወላጆች የሆኑት በራካና ኢዩ፥ ዝነኛ ወታደር የነበረው፥ በኋላም የሠላሳዎቹ ኀያላን መሪዎች ከሆኑት አንዱ የሆነው፥ የገባዖን ተወላጅ ዩሽማዕያ፥ የገዴራ ተወላጆች የሆኑት ይርመያ፥ ያሕዚኤል፥ ዮሐናንና ዮዛባድ፥ የሐሪፍ ተወላጆች የሆኑት ኤልዑዛይ፥ ያሪሞት፥ በዓልያ፥ ሸማርያና ሸፋጥያ፥ ከቆሬ ጐሣዎች የሆኑት ኤልቃና፥ ዩሺያሁ፥ ዐዛርኤል፥ ዮዔዜርና ያሸብዓም፥ የገዶር ተወላጆች የሆኑት የይሮሐም ልጆች ዮዔላና ዘባድያ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አለቃቸውም አኬዘር ነበረ፤ የጊብዓዊው የሰማዓ ልጅ ኢዮአስ፥ የዓዝሞት ልጆች ኢዮኤልና ፋሌጥ፥ በራኪያና ዓናቶታዊው ኢዩ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አለቃቸው አሒዔዝር ነበረ፤ ከእርሱም በኋላ ኢዮአስ፥ የጊብዓዊው የሸማዓ ልጆች ይዝኤል፥ ፋሌጥ፥ የዓዝሞት ልጆች በራኪያ፥ ዓናቶታዊው ኢዩ፥ |
ከእርሱ ዘሮች ሰባት ወንዶች ልጆች ይሰጠን፤ እኛም ከጌታ በተመረጠው በሳኦል አገር በጊብዓ በጌታ ፊት እንስቀላቸው” ብለው መለሱለት። ስለዚህ ንጉሡ፥ “እሺ! እሰጣችኋለሁ” አለ።